የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
Ethiopian Revenues and Customs Authority
Pay your tax today for a better tomorrow
 
Revenue Web  
 
Main menu
  Customs
  Domestic Tax
  library
  Proclamation
  Regulation
  Directives
  Declaration Forms
  Duty Free and Investment
  Documentation
  AEO
  Business Community
  Ethiopian Diaspora

 
Vacancy
.
Bid info
.
Tools
  Tax Calculation
  Search Hs Code
  Prevent Corruption
  Import/Export Information

 
Online Services
* Sales Registration Machine Report
 
* E-Tax
* Purchase Declaration

 


 
.

የክፍት ሥራ መደብ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገቢዎችን ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋናው መ/ቤትና በሥሩ በሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶች በሚገኙ 1600 ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ለክፍት ሥራ መደቦቹ የሚያመለክቱ ሥራ ፈላጊዎች፡-

 • ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በ2006 የትምህርት ዘመን የተመረቁ፤
 • በመደበኛ የትምህርት ፕሮግራም ተምረው ያጠናቀቁ፤
 • የተጠቃለለ የመመረቂያ ነጥባቸው ቢያንስ ወንዶች 2.5 እና ሴቶች 2.2 ያላቸው እና
 • በአካውንቲንግ፤ በኤኮኖሚክስ፤ በማኔጅመንት፤ በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን፤፤ በዓለምአቀፍ ንግድና ኢንቨስትመንት፤ በሕግ፤ በታክስና ጉምሩክ አስተዳደር፤ በኮምፒዩተር ሣይንስ የሙያ መስክ የተመረቁ መሆን አለባቸው፡፡

ስለሆነም ሥራ ፈላጊዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስት ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉ ስድስት ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን ምዝገባ ይካሄዳል) ውስጥ፡-  

 • በአዲስ አበባ በሚገኙ ዋናው መ/ቤት እና ቅ/ጽ/ቤቶች መቀጠር የሚፈልጉ ሥራ ፈላጊዎች መገናኛ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ መ፤
 • ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ በሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶች መቀጠር የሚፈልጉ ሥራ ፈላጊዎች መቀጠር በሚፈልጉበት የባለሥልጣኑ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመዘገቡ እያሳሰብን፤ ቅ/ጽ/ቤቶቻችን በመቀሌ፤ በባሕርዳር፤ በሚሌ፤ በጋላፊ፤ በኮምቦልቻ፤ በጅግጅጋ፤ በድሬዳዋ፤ በሞያሌ፤ በጅማ፤ በሀዋሳ፤ በአዳማ እና በሞጆ የሚገኙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሥራ ፈላጊዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት ያለባቸው ሲሆን የአዲስ አበባ አመልካቾች ቀጥሎ በተመለከተው የምዝገባ ፕሮግራም መሰረት ብቻ የሚመዘገቡ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡
የሥራ ፈላጊዎች የምዝገባ ፕሮግራም


ተ/ቁ

ስማቸው የሚጀምርበት የእንግሊዝኛ ፊደል

የምዝገባ ቀን

1

A B C D የሆኑ

በ6/12/06

2

E F G H የሆኑ

በ7/12/06

3

I J K L M የሆኑ

በ8/12/06

4

N O P Q የሆኑ

በ9/12/06

5

R S T U የሆኑ

በ10/12/06

6

V W X Y Z የሆኑ

በ11/12/06

ማሳሰቢያ፡-

  • ሥራ ፈላጊዎች መመደብ የሚፈልጉበትን አንድ ቦታ ብቻ በሥራ መጠየቂያ ቅፅ ላይ በግልፅ ማመልከት አለባቸው፡፡
  • የፈተና ቀን፤ ቦታና ሰዓት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዋናው መ/ቤትና ቅ/ጽ/ቤቶች የሚያመለክቱ ወደፊት አመቺና ተደራሽ በሆነ መንገድ የሚገለጽ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶች ለመቀጠር የሚያመለከቱ ሥራ ፈላጊዎች ቅ/ጽ/ቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  • ክፍት የሥራ መደቡ ፆታ አይለይም፡፡
  • ሴቶች ይበረታታሉ፡፡
  • ከምዝገባ ፕሮግራማቸው ውጭ የሚመጡ አመልካቾች አይስተናገዱም፡፡
 
ERCA Chat
 
Poll
 
Please comment on our vacancy page

Excellent
V.Good
Good
Needs Improvement

 
 
Latest Event
 
No Upcoming Event

 
 
 
Site Map
If you have any comment on the web site, please contact the web master - ercawebadmin@revenue.gov.et or ercawebauthor@revenue.gov.et
© 2012 Ethiopian Revenues and Customs Authority. All right reserved.