የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የልዩ ልዩ ንብረቶች ዝግ ጨረታ ማስታወቂያ 01/2009 ዓ.ም

Posted in BID

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነታቸው የምስ/አ/አ/መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት እና የአዲስ ከተማ ክ/ከ//አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት የሆኑ የሚጠበቅባቸውን የግብር/ታክስ ዕዳ ባለመክፈላቸው ምክንያት በዋና መ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ ፤ ንብረትነታቸው የጌታነህ ትሬዲንግ የሆኑ የተለያዩ አልባሳቶች እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እንዲሁም ህጋዊ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ሳይፈጸምባቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የተወረሱ ተሽከርካሪዎችን እና የብር ጌጣጌጦችን፣በሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተወርስው የሚገኙ የተለያዩ የህንጻ መሳሪያዎች፣ፈርኒቸር፣ሌክትሮኒክስ፣የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣የፈብሪካ ግብአት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣በድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ አልባሳቶች እንዲሁም በሞያሌ ገ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ተወርስው የሚገኙ የተለያዩ አልባሳቶች፣የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች እና ኤሌክትሮኒክሶችንበዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም

1.  በጨረታው ሽያጭ ስርዓት በጉምሩክ ለተወረሱ ንብረቶች ለመወዳደር የሚፈልግ ማኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና ንግድ ፈቃድ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ  እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ  የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡

2.  በዋና መ/ቤት በታክስ ዕዳ ተይዘው ጨረታ ላይ ለቀረቡ ንብረቶች ንግድ ፈቃድ እና ቫት ተመዝጋቢ መሆን ሳያስፈልግ ከ18 ዓመት በላይ የሆነና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ መጫረት ይቻላል፡፡

3.  ተጫራቶች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ከሠዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ሰዓት  እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በዋና መ/ቤት  ሕንጻ ሐ 1ኛ ፎቅ የተያዙና የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት፤ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ  የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

4.  በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ ሀያ በመቶ (20%) ለጨረታ ዋስትና( CPO) በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ሲፒኦውም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን  ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

5.  ተጫራቾችበሚከተለው የጨረታ ቀናት(ስኬቹል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተቁ

 

የጽ/ቤቱ ስም

 

የጨረታው አይነት

 

የንብረት የመመልከቻ ቀንጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ

 

የጨረታው የመዝጊያና የመክፈቻ ቀንና     ሰዓት

 

1

 

ዋ/መ/ቤት

ዝግ

እስከ  16/12/2009

ነሀሴ 17/2009   3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡

2

 

ሞጆ ገ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ዝግ

እስከ  15/12/2009

ነሀሴ 16/2009   3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡

3

ድሬዳዋ ገ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ዝግ

እስከ  13/12/2009 6፡00 ድረስ

ነሀሴ 15/2009   3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡

4

 

ሞያሌ ገ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ዝግ

እስከ  11/12/2009

ነሀሴ 12/2009 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡

1.  በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው ዋጋ የሚሠጡበት ቅፅ ከጨረታሠነዱ ጋር የተያያዘ ሲሆን በቅፆቹ  መሠረት ለሚወዳደሩበት ንብረት ዋጋ የተሰጡበት፤ የተጫራቾች ስም አድራሻ ፊርማ፣እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም  በዋናው መ/ቤት ህንፃ ‹‹ሐ››1ኛ ፎቅ   ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታውም በዋናው መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ፡፡

2.  ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡

3.  ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡

4.  አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

5.  አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈጸሙ በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል፤

6.  ከላይ በተ/ቁ 10 እና በተ/ቁ 11 በተገለጹት  ቀናት  ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና  ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት  እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

ባለሥልጣኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃበስልክ ቁጥሮች ዋ/መ/ቤት- 011667-3795፣ ሞያሌ-046-444-0382፣ ሞጆ 022-236-0190፣ ድሬዳዋ 025-112-49 28 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Visitors: Yesterday 6 | This week 1 | This month 2203 | Total 824986

We have 378 guests and no members online