FAQ

Posted in FAQ

የሽያጭመመዝገቢያ መሳሪያ /Cash Register Machine/ ተጠቃሚዎች ማሽኑ ብልሽት ሲያጋጥመው መብራት በሚጠፋበት ወቅት እንዲሁም የአድራሻ ለውጥ በሚያደርጉበት ጊዜ ያለው አጠቃላይ መረጃ ቢብራራ?

የሽያጭመመዝገቢያ መሳሪያው ብልሽት በሚያጋጥምበት ጊዜ ለአገልግሎት ማዕከሉ እና ለባለስልጣን መ/ቤቱ በ2 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ መብራት በሚጠፋበት ጊዜ ለባላስልጣን መ/ቤቱ ወድያውኑ በስልክ ወይም በአካል ማሳወቅ፣ አድራሻ ለውጥ በሚፈልጉ ጊዜ አድራሻ ለውጥ ያደረጉበትን ንግድ ፈቃድ እና መመልከቻ በማያያዝ ለባለስልጣን መ/ቤቱ ማቅረብ ያለባቸው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የወጭ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ ክሊራንስ በክፍሎች ይሰጣል?

ተማሪዎች ለእንግልት እና ለተጨማሪ ወጪ ሳይዳረጉ አገልግሎት ከሰጡበት ተቋም የሚፈለግባቸውን ክፍያ /አገልግሎት/ ስለማጠናቀቃቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ሰጽፈው ሲቀርቡ በአካባቢያቸው ከሚገኘው ገቢ ሰብሳቢ ቅ/ጽ/ቤት ክሊራንስ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገለፃለን፡፡

የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኃላ በምን ያህል ጊዜ ገንዘብ መክፈል እንደሚገባ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር እንዲሁም አጠቃላይ ያለው ሁኔታ በዝርዝር ቢገለጽ?

የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ /cost sharing/ በተመለከተ ከአንድ ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኃላ ክፍያው መጀመር ያለበት ሲሆን፤ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር በጤናና በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡበትንና አገልግሎት የሰጡበትን ማስረጃ በማቅረብ ወደሚገኘው ገቢ ሰብሳቢ ቅ/ፅ/ቤት በመሄድ መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ወደ ውጭ ምርቶቻቸውን የሚልኩ ባለሃብቶች በሚልኩበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 0% ሆኖ ሳለ ቫት/VAT/ ተመዝጋቢ የመሆናቸው ምክንያት በግልጽ ቢብራራ?

ወደ ውጪ ምርቶቻቸውን የሚልኩ ባለሃብቶች የዜሮ ተመን ቫት ተመዝጋቢ የመሆናቸው ምክንያት ለግብዓት የተከፈለውን ታክስ ተማላሽ ለማድረግና የውጭ ንግዱን ከማበረታታት አንፃር ነው፡፡

ቅጣት ብቻ የተጣለበት ግብር ከፋይ ቅጣት እንዲነሳለት በሚጠይቅበት ጊዜ ስንት መቶኛ ይነሳለታል?

አስተዳዳራዊ መቀመጫዎች እንደማይነሱ ከተገለፁት ሁኔታዎች በስተቀር በግብርና ታክስ ላይ የተጣሉ አስተዳደራዊ መቀመጫዎች እንደሁኔታው በሙሉ ወይም በከፊል ሊነሱ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆኖ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ የሌለው ሰው በሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ላይ ምን ያህል % ነው ግብር የሚከፍለው?

ቅድመ ግብር ክፍያ ቀንሰው እንዲስቀሩ ሀላፊነት የተጣለባቸው አካላት አገልግሎቱን ያቀረቡ ሰዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከሌላቸው 30% (ሰላሳ ፐርሰንት) ቀንሰው ገቢ እንዲያደርጉ በህጉ ተደንግጓል፡፡

የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች /ተቋማት/ ለአምልኮ መገልገያ የሚሆን ህንፃ በሚገነቡበት ወቅት ለግንባታ ስራ የሚያገለግሉ እቃዎችን ሲገዙ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከተርንኦቨር ታክስ ነፃ ናቸው ወይስ ይከፈሉበታል?

የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ የሚሆን ህንፃ በሚገነቡበት ጊዜ ታክሱን ሳይጨምሩ ግብይት ይፈፅማሉ የሚል ህግ ስለሌለ እንደማንኛውም ሸማች/ገዥ ታክሱን ጨምረው ዕቃዎችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

በጥቃቅንና አነስተኛ ተሰራጅተው በንግድ ስራ የተሰማሩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸውን?

በጥቃቅንና አነስተና ተደራጅተው በንግድ ስራ የተሰማሩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ አይደሉም፡፡

ከህንፃ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ ላይ ስለሚከፈል የካፒታል እድገት/Capital Gain/ ታክስ ጋር በተያያዘ ያለው የታክስ አከፋፈል ምን ይመስላል?

ጥቅም ላይ 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) ግብር የመከፈልበት መሆኑ በህጉ ተደንግጓል፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ለማግኘት መሟላት ያሉባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

በባለስልጣኑ የተዘጋጀውን ቅፅ ሞልቶ ማቅረብና የጣት አሻራ መስጠት፣

የንግድ ስራ ፈቃድ ለማውታት የግብር ከፋይ መለያ ቁትር የምስክር ወረቀት ከባላስልጣኑ በቅድሚያ ማግኘት፣

ግለሰቡ የተለያየ የንግድ ዘርፍ ወይም ቅርንጫፍ በተለያየ ቦታዎች ቢኖሩትም አንድ የግብር ከፋይ መሌ ቁትር ብቻ የማውጣት ግዴታ አለበት፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ጋር በተያያዘ የምዝገባ ለውጦ፣ የአድራሻ ለውጥ፣ እንዱሁም ምትክ የግብር ከፋዩ መለያ ቁጥርየምስክር ወረቀት ለማግኘት ያሉት ቅድመ ሁኔዎች በዝርዝር ቢገለጹ?

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የምዝገባ ለውጦችና ማሻሻያዎችን በተመለከተ ለውጡ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ለተመዘገበበት ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ማሳወቅ፤ መረጃዎች የሚያስለውጥ ከሆነ የቀድሞውን የምስክር ወረቀት መመለስ፣ ምትክ የግብር ከፋ መለያ ቁጥር ለማግኘት፣ ግብር ከፋዩ ለፖሊስ ያሳወቀበትን ማስረጃ ካቀረበ፣ ወይም የምስክር ወረቀቱ በተለያየ ምክንያቶች ከተበላሸ ግብር ከፋ ሲመለክት የተበላሸውን መልሶ ሌላ ታትሞ ይሰጠዋል፡፡

በኢትጵያ ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ ለተሰጠ የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ ላይ ምን ያህል ፐርሰንት ግብር ይከፈልበታል?

በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ ለተሰጠ የቴክኒክ አገልግሎት የተፈፀመ ክፍያ 10% (አስር በመቶ) ብር የሚከፍልበት መሆኑን በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 32 ላይ ተደንግጓል፡፡

የውጭ ሀገር ዜጋ ከ183 ቀናት በላይ በመመላለስም ሆነ ሀገር ውስጥ በሚቆበት ጊዜ የግብር ከፋዩ መለያ ቁጥር /TIN/ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ቢዘረዘሩ?

የውጭ አገር ዜጋ ከ183 ቀናት በላይ በመመላለስም ሆነ እዚሁ በመቀመጥ በሚቆይበት ጊዜ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡-

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ፣

ፓስፖርት፣

ቪዛ አንዲሁም

ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የመኖሪያ ፈቃድ ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡

በኢንቨስትመንት ፈቃድ ላይ ያሉ ድርጅቶች ግብር እንዴት ማሳወቅ እንደሚገባ እንዲሁምየእፎይታ ጊዜ ቢገለጽ?

በኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተው በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች የግብ ትያቄ የሚነሳባቸው የንግድ ፈቃድ ሲያወጡ ነው፡፡ የእፎይታን ጊዜ በተመለከተ በተሰማሩበት ዘርፍና  የኢንቨስትመንት ስራው በሚከናወንበት አካባቢ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡

በግብርና ምርት /አርሶ አደሩ ያመረተውን ሲሸጥ/ ዊዝ ሆልድ ይደረጋል?

አርሶ አደሩ ያመረተውን ለተጠቃሚ ስለሚሸጥ እና በንግድ ስራ ላይ ያልተሰማራ ስለሆነ ዊዝሆልድ አይደረግም ነገር ግን በግብርና ስራ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥቶ ወደ ንግድ የገባ ከሆነ ዊዝ ሆልድ ይደረጋል፡፡

የህብረት ስራ ማህበራት አመታዊ የስራ ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል; ካቀረቡስ የሂሳብ የሂሳብ ጊዜቸው ከመቼ እስከ መቼ ነው?/በገቢ ግብር አዋጅ ተለይቶ አልተጠቀሰም/

የህብረት ስራ ማህበራት በአዋጅ ቁጥር 147/1991 የተቋቋሙ ሲሆን፤ አመታዊ የስራ ሪፖርት ማቅረብ የጠበቅባቸዋል፤ የሂሳብ ጊዜያቸውን በተመለከተ የደረጃሀ ግብር ከፋዮች በመሆናቸው ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 ነው፡፡

የውሎ አበል ክፍያ እንዲሁም የመዘዋወሪያ አበል ክፍያ ከግብር ነጻ የሚሆነው በምን መልኩ ነው?

የውሎ አበል አንድ ሰራተኛ የተቀጠረበትን ስራ ለማከናወን የቀን የውሎ አበል ከግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 225 ወይም ከደሞዙ 4ፐ (አራት ፐርሰንት) ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን በላይ ሊሆን ኤችልም፡፡ የመዘዋወሪያ አበልን በተመለከተ ከጠቅላላ የወር ደመወዝ ¼ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የመዘዋወሪያ አበል በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2200 መብለጥ አይችልም፡፡

መኖሪያ ቤት ለቢዝነስ ሲከራይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆኑን /አለመሆኑን ቢገለጽልን?

የመኖሪያ ቤት ለንግድ ከተከራየ ከመኖሪያ ቤትነት ወደ ንግድ ቤት ስለተቀየረ ማናቸውም ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች ይመለከተዋል፡፡ በዚህ መሰረት አመታዊ ገቢው ከ500ሺ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግዴታ ተመዝጋቢ ይሆናል፡፡

በቅድሚያ ክፍያ /Advanced Payment/ ስርአት የእቃና የአገልግሎት ግዥ ሲፈጸም የቅድሚያ ታክስ ክፍያ /withholding tax/ የሰበሰባል ወይስ አይሰበሰብም?

በቅድመ ክፍያ/Advanced payment/ ስርዓት የዕቃና አገልግሎት ግዥ ሲፈፀም ግብሩን ቀንሶ ገቢ ማድረግ ያለበት ሰው ቅድመ ታክሱን ቀንሶ ማስቀረት የሚገባው ዕቃ አቅራቢው ወይም አገልግሎት ሰጪው በሚያቀርበው ዕቃ ወይም አገልግሎት በተፈፀመው ስራ /invoice/ ልክ እና ወቅት መሆን አለበት፡፡

የምግብ እህል /ጤፍ፣ ስንዴ…ወዘተ/ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው?

የምግብ እህሎችን ዋጋ ለማረጋጋት መንግስ ከመጋቢት 10/2000 ዓ.ም ጀምሮ ከአጠቃላይ ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች ማለትም ከተርንኦቨር ታክስና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርጓል፡፡

በኮንስትራክሽን ስራ ላይ ለሚያዝ ሪቴንሽን ቫት ይሰበሰባል ወይስ አይሰበሰብም?

በኮንስትራክሽን ስራ ላይ በያዣ ገንዘብ /Retention/ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ አልተደረገም፡፡

ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አክሲዮን ማህበር ልዩነታቸው፣ አንድነታቸው እንዲሁም የግብር አከፋፈላቸው እንዴት እንደሆነ በግልፅ ቢቀመጥ?

ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አክሲዮን ማህበር አንድነታቸው፡- ሁለቱም እንደ ድርጅት ካገኙት ገቢ ላይ 30ፐ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል በሚኖርበት ጊዜ 10% ግብር የሚከፍሉ ሲሆን፣ ልዩነታቸው በአደረጃጀት ማለትም በግለሰቦች ብዛትና በካፒታል መጠናቸው ነው፡፡

በተለያዩ ቦታ የተለያዩ የንግድ ዘርፎች ያላቸው ግብር ከፋች ግብራቸውን እንዴት አጣምረው መክፈል እንዳለባቸው እና የት መክፈል እንዳለባቸው በግልፅ ቢብራራ?

ግብር ሀፋዩ በአንድ ሰንተረዥ ስራ ግብር የሚከፈለበት ገቢ ከተለያዩየገቢ ምንጭ የሚገኝ ከሆነ ግብሩ የሚወሰነው ገቢውን ወደ አንድ በማጠቃለል ሲሆን፣ ግብሩ የሚከፈልበት ቦታን በተመለከተ ዋናው ምዝገባ በተደረገበት ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ይሆናል፡፡

በኮንስትራክሽን ስራ ላይ በረዥም ጊዜ ውል ላይ መከፈል ስላለበት የገቢ መጠንና የክፍያ ጊዜ መቼና እንዴት እንደሆነ በቂ ማብራሪያ ቢሰጠን?

ለረዥም ጊዜ ከሚቆይ የንግድ ስራ ውል ጋር በተያየዘ አንድ ሂሳብ በገቢ ውስጥ መቼ እንደሚካተት ወይም ተቀናሽ እንደሚደረግ የሚወሰነው በአንድ የግብር ዘመን ውስጥ ከውሉ ውስጥ የተጠናቀቀውን በመቶኛ በማስላት መሆን እንዳለበት በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 63 ላይ ተደንግጓል፡፡

በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተርንኦቨር ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ግብር ከፋዮች ተርንኦቨር ታክስ እያሳወቁ ቆይተው አመታዊ ግብራቸውን ለማሳወቅ በሚሄዱበት ጊዜ ከመ/ቤቱ አመታዊ ገቢያቸው ከ500ሺ ብር በላይ እንደሆነ በመግለፅ VAT ሰርተፍኬት ታትሞ የሚሰጣቸው ሲሆን ወደኋላ ተመልሶ ቅጣትና ወለድ እንዲከፈል መጠየቁ አግባብ ነውን?

በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ታክስ ከፋዩ የሚከናውነው ታክስ የሚከፈልበት ሽያጭ ከብር 500ሺህ በላይ ይሆናል ብሎ ለመገመት የሚያስችል ሽያጭ ከብር 500ሺ በላይ ሆናል ለመገመት የሚያስችል ተጨባጭ ምክንያት ያለው እንደሆነ መመዝገብ ያለበት ሲሆን፣ አንድ ግብር ከፋይ በአንድ ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርንኦቨር ታክስ ተመዝጋቢ ሊሆን ስለማይችል የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው ተርን ኦቨር ታክስ ሲከፍሉ የቆዩ ከሆነ መከፈል ያለበት በልዩነት መሆን አለበት፤ ቅጣትና ወለዱን በተመለከተ መመዝገብ ከነበረባቸው ጊዜ ጀምሮ የሚጣልባቸው ሲሆን፣ ባለስልጣኑ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ ያለበት ሆኖ ነገር ግን የምዝገባ ማመልከቻ ያላቀረበን ሰው ራሱ በመመዝገብ ለተመዘገበው ሰው የምዝገባ ሰርተፍኬት መላክ የሚችል መሆኑ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 6 ላይ ተደንግጓል፡፡

end faq

አዲስ አስመጭ ነኝ እቃ ለማስመጣት በጉምሩክ ረገድ ምን ምን ማሟላት አለብኝ?

 • በጣት አሻራ የተደገፈ ቲን/Tin/ ማውጣት፣
 • የአስመጭነት ንግድ ፈቃድ ከንግድ ሚኒስቴር ማውጣት፣
 • የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን፣ትራንዚተር መቅጠር ሲሆን

ወደ ጉምሩክ ሲመጡ የሚከተሉትን ሰነዶች አሟልተው መቅረብ አለባቸው፣

 • የባንክ ፈቃድ፣
 • የማጓጓዣ ሰነድ፣
 • የዋጋ ሰነድ፣
 • የዕቃ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ፣
 • የስሪት ሀገር የምስክር ወረቀት::

ኤክስፖርት በሚደረጉ እቃዎች ላይ ምን ምን አይነት ቀረጥና ታክስ ይከፈላል?

ኤክስፖርት በሚደረጉ ዕቃዎች ላይ በከፊል ከተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ በቀር ሌሎች ምርቶች ምንም ዓይነት ቀረጥና ታክስ አይከፈልባቸውም::

አምራቾች ነን ከዉጭ ለምናስገባዉ ጥሬ ዕቃ የቀረጥ ቅናሽ /ሁለተኛመደብ/ ተጠቃሚ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን? ማንን ነዉ የምጠይቀዉ?

በመጀመሪያኢንዳስትሪ ሚኒስቴር በመሄድ የድጋፍ ደብዳቤ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር በማፃፍ ገንዘብና ኢኮኖሚ ተገቢነቱን ያመነበት ከሆነ የሁለተኛ ደረጃ ተጠቃሚነት ፈቃድ በመስጠት  ዝርዝሩን ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ለዋጋና ታሪፍ አሰራርና ፕሮግራም ልማት ዳይሬክተር ያሳውቃል በዚያ መሰረትም ዋጋና ታሪፍ አሰራርና ፕሮግራም ልማት ዳይሬክተር ግብዓቶች በተፈቀደው መልኩ እንዲገቡ ዝርዝራቸውን ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ያሳውቃል፡፡ 

በመጀመሪያኢንዳስትሪ ሚኒስቴር በመሄድ የድጋፍ ደብዳቤ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር በማፃፍ ገንዘብና ኢኮኖሚ ተገቢነቱን ያመነበት ከሆነ የሁለተኛ ደረጃ ተጠቃሚነት ፈቃድ በመስጠት  ዝርዝሩን ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ለዋጋና ታሪፍ አሰራርና ፕሮግራም ልማት ዳይሬክተር ያሳውቃል በዚያ መሰረትም ዋጋና ታሪፍ አሰራርና ፕሮግራም ልማት ዳይሬክተር ግብዓቶች በተፈቀደው መልኩ እንዲገቡ ዝርዝራቸውን ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ያሳውቃል፡፡ 

በቦንድድ መጋዘን የገቡ እቃዎች የመጋዘን ቆይታ ጊዜ ምን ያህል ነዉ?

ወደጉምሩክቦንድድ መጋዘን የገባ ማናቸውም የንግድ ዕቃ ወደ መጋዘን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በ4 ወር ጊዜ ውስጥ አስፈላጊው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞበት ከመጋዘን መውጣት ያለበት ሲሆን ወደ ጉምሩክቦንድድ መጋዘን የገባ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ ምርቶች ማምረቻ የሚውል መሳሪያ፣ መለዋወጫ እና ግብዓት ወደ መጋዘን ከገባበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞበት ከመጋዘን መውጣት አለበት፡፡

ቀረጥና ታክስ ስለበዛብኝ በተለያየ ጊዜ ለመክፈል የክፍያ ጊዜ ስምምነት ሊሰጠኝ ይችላል?

የክፍያ ጊዜ ስምምነት የሚመለከታቸው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው::

I. በልዩነትየሚፈለግ ቀረጥና ታክስ ክፍያ እንዲከፍል የውሳኔ ማስታወቂያ ለደረሳቸው ባለዕዳዎች፣

II. ላልተከፈለየቀረጥና ታክስ ዕዳ ለማዋል ንብረታቸውን ለተያዘባቸው ወይም ንብረታቸውን ለመሸጥ ሀራጅ ከወጣ በኋላ ለመክፈል ፈቃደኛ ለሆኑ ባለዕዳዎች፣

III. ህግንበመተላለፍ የተያዙ ተሽከርካሪዎች እና ቀረጥና ታክስ የሚፈለግባቸው ባለዕዳዎች ሲሆን ቀረጥና ታክስ በዛብኝ ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ስለማይካተት የክፍያ ጊዜ ስምምነት የማይመለከታቸው መሆኑ ይታወቅ፡፡

በቦንድድ መጋዘን ለምሸጣቸዉ መኪኖች ቫት/VAT/ መሰብሰብ ይጠበቅብኛል?

በቦንድድመጋዘን ለምንሸጣቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መሰብሰብን በተመለከተ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎበት የሚሸጡ ዕቃዎች/ተሸከርካሪዎች ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መሰብሰብ የሚጠበቅብን ሲሆን ነገር ግን ዕቃዎችን/ተሸከርካሪዎችን ለቀረጥ ነፃ ተጠቃሚዎች ወይም ባለመብቶች የምንሸጣቸው ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መሰብሰብ አይጠበቅብንም፡፡

ዉጭ ሀገር ቆይቼ ወደ ሀገሬ እየተመለስኩ ነዉ ይዤ መግባት የምችለዉ እቃዎች ምን ምን ናቸው? በቀረጥ ነፃስ እችላለሁ?

ውጭሀገር ቆይተው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ዜጎች የግልና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ያለውጭ ምንዛሬ ክፍያ ከነበሩበት ሀገር ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጠቅልለው ስለመግባታቸው የሚገልፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ማስረጃ በመያዝ ዕቃዎቹን ቀረጥና ታክስ ከፍለው ማስገባት የሚችሉ ሲሆኑከቀረጥ ነፃ ማስገባት የማይቻል መሆኑ እንገልፃለን፡፡

ተመላሽ ኢትዮጲያዊ ነኝ የግል አዉቶሞቢል ከቀረጥ ነጻ ይዤ መግባት እችላለሁ? ፒካፕ/ሲንግልካፕ/ ቢሆንስ?

በውጭአገር የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ውስጥ አገልግለው የሚመለሱ ዲፕሎማቶች አንድ የግል ተሽከርካሪ ከቀረጥ ነፃ ማስገባት የሚፈቀድላቸው ሲሆን ሌሎች ተመላሽ ኢትዮጵያን ግን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት የማይችሉ መሆኑ የተደነገገ ሲሆን ነገር ግን ውጭ ሀገር አምስት አመትና ከዚያ በላይ ቆይተው ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አንድ የግል አውቶሞቢል ቀረጥና ታክስ በመክፈል ማስገባት ይችላሉ፡፡

ኢትዮጲያ ዉሥጥ ነዋሪ ነኝ በግሌ የግል መገልገያ መኪና ገዝቼ ማስገባት ፈልጌ ነበር ይቻላል?

በሌሎችአስመጪዎች በኩል ካልሆነ በቀር የአስመጪነት ፈቃድ ሳይኖር የግል መገልገያ መኪና ማስመጣት አይቻልም፡፡

የግል ቤቴን በመገንባት ላይ ነኝ የፊኒሽንግ እቃዎችን ከዉጭ አገር ገዝቼ ከረጥ ነፃ ማስገባት ስለምፈልግ የሚፈቀድልኝ ምን ምን ዕቃዎች ናቸው?

ምንምአይነት የፊንሽንግ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ ማስመጣት አይቻልም፡፡

አዲስ የንግድ እቃ አስመጭ ነን እቃ በምናስጭንበት ወቅት ኤሪያ ኮድ ከጉምሩክ አምጡ በምንባልበት ወቅት እንዴት ማግኘት እንችላለን?

ኤሪያልኮድ በመልቲ ሞዳልም ሆነ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ለሚመጡ ጭነቶች አስፈላጊ አይደለም ተብሎ በባህርና ትራንዚት ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት በኩል ስለተላለፈ አስፈላጊ አይደለም በዚህ ቦታ ቲን ብቻ በL/C condition ላይ መካተቱ በቂ ነዉ፡፡

ያለ ንግድ ፈቃድ ወደ ዉጭ መላክ የምንችለዉ በርበሬ መሰል የምግብ እህሎች መጠን ምን ያህል ነዉ?

ያለንግድ ፈቃድ ወደ ውጭ ተጓዦች ከኢትዮጵያ ይዘው እንዲወጡ የተፈቀዱ የግብርና ምርቶችና የፋብሪካ ውጤቶች መጠን እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡-

ቡናን በተመለከተ(ጥሬ ወይም የተቆላ ወይም የተፈጨ ቡና)

ኤክስፖርት ስታንዳርድ ያልሆነ ቡና በሚከተለው መጠን ይዘው መውጣት ይችላሉ                                     

 • ነዋሪነታቸው በውጭ ሀገር የሆነና በአገር ውስጥ ቆይታ አድርገው የሚመለሱ ከሆነ በግለሰብ ደረጃ 3 ኪሎ ግራም እና በቤተሰብ ደረጃ እስከ 5 ኪሎ ግራም ይዘው መጓዝ ይችላሉ፡፡
 • ለተለያዩ የስራ ጉዳዮች ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ወደ ውጭ አገር የሚጓዙ ከሆነ በግለሰብም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ እስከ 2 ኪሎ ግራም ቡና ይዘው መጓዝ ይችላሉ፡፡
 • የስራቸው ፀባይ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ምልልስ ያደረጉ ከሆነ በጉዟቸው እስከ 1 ኪሎ ግራም ቡና በግለሰብም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ይዘው መጓዝ ይችላሉ፡፡

ከቡና ውጭ ያሉ ሌሎች የግብርና ምርቶችና የፋብሪካ ውጤቶችን በተመለከተ

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ተመላላሽ ላልሆነ ተጓዥ/አጓጓዥ

ተመላላሽ ለሆነ ተጓዥ/አጓጓዥ

1

የተፈጨ በርበሬ

በኪሎ ግራም

10

5

2

የተዘጋጀ ቅመማ ቅመም ከየዓይነቱ

በኪሎ ግራም

5

4

3

ሽሮ

በኪሎ ግራም

10

5

4

የጤፍ ዱቄት

በኪሎ ግራም

5

-

5

የተዘጋጀ ቅቤ

በኪሎ ግራም

5

2

6

ቆሎ

በኪሎ ግራም

8

4

7

ማር

በኪሎ ግራም

3

2

8

የባህል አልባሳት ከየዓይነቱ

በቁጥር

15

5

9

የባህል ጫማዎች

በጥንድ

10

5

10

ባህላዊ ያልሆኑ ጫማዎች

በጥንድ

5

2

 

  ወደ ጅቡቲ፣ሶማሊያ፣ኬኒያና ሱዳን  አገሮች የሚጓዙ መንገደኞች ለአንድ ጉዞ 3 ኪሎ ግራም ጫት ይዘው መጓዝ ይችላሉ፡፡

የዉጭ ዜጋ ነኝ የስራ ፈቃድ አዉጥቻለሁ የግል መገልገያ መኪናየን ማስገባት እፈልግ ነበር እችላለሁ?

አይቻልም::

ከቀረጥ ነጻ ያስገባነዉን መኪና ቀረጥና ታክስ መክፈል ፈልገን ነበር በተለያየ ጊዜ መክፈል እንድንችል የክፍያ ጊዜ ስምምነት ይፈቀድልናል?

የክፍያ ጊዜ ስምምነት የሚመለከታቸው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው

I. በልዩነትየሚፈለግ ቀረጥና ታክስ ክፍያ እንዲከፍል የውሳኔ ማስታወቂያ በደረሳቸው ባለዕዳዎች፣

II. ላልተከፈለየቀረጥና ታክስ ዕዳ ለማዋል ንብረታቸውን ለተያዘባቸው ወይም ንብረታቸውን ለመሸጥ ሀራጅ ከወጣ በኋላ ለመክፈል ፈቃደኛ ለሆኑ ባለዕዳዎችና

III. ህግንበመተላለፍ የተያዙ ተሽከርካሪዎች እና ቀረጥና ታክስ የሚፈለግባቸው ባለዕዳዎች ሲሆን በቀረጥ ነፃ የገቡ መኪናዎችን ቀረጥና ታክስ መክፈል ለሚፈልጉ ሰዎች የክፍያ ጊዜ ስምምነት ተፈፃሚነት የለውም፡፡

አዲስ ፋብሪካ ገንብተናል ለመጀመሪያ ለሙከራ ምርት ጥሬ ዕቃ ያለ ዉጭ ምንዛሬ ክፍያ ያለ ቀረጥ ማስገባት ይፈቀድልናል?

አግባብነትካለዉ የመንግስት አካል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያገኙ ከሆነና በዉጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ወይም የዉጭ ሃገር ባለሃብቶች ከሆኑ ከተሰማሩበት የኢንቨስትመንት ስራ ተዛማጅ ለሙከራ ምርት የሚበቃ ጥሬ እቃ በተፈቀደዉ መጠን ማስገባት ይችላሉ፤የቀረጥ ነፃ መብቱን ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ማስፈቀድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ (መ.ቁ.66/2004 /ሠንጠረዥ ቁ.14)

ዕቃዎችን በዶኔሽን ለማስገባት ማሟላት ያለብን ነገር ምንድን ነዉ?/ከትምህርትቤቶች አንጻርና ከNGO አንጻርስ/

ትምህርትቤቶች ለትምህርት ስራቸዉ ብቻ የሚያገለግሉ የስጦታ እቃዎችን ከዉጭ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን መጠኑ ለንግድ የማይዉል ሆኖ ከተቋሙ ወይም ድርጅቱ ተግባራት ጋር በታቀደዉ መጠን ይሆናል፤ቀረጥና ታክስ ይከፈልበታል፡፡(መ.ቁ. 66/ሠንጠረዥ9/)

መሟላትያለበት ቅድመ ሁኔታ፡- የስጦታ ምስክር ወረቀት የተረጋገጠ እና ድርጅቱ የተቋቋመበት ሰነድ፡፡

የበጎአድራጎት ድርጅቶች በስጦታ ያገኙትን ከስራቸዉ ጋር የተያያዙ ዕቃዎችን ያለዉጭ ምንዛሪ ፍቃድም ሆነ በቀረጥ ነፃ ለማስገባት የሚችሉ ሲሆን ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ፡- (መ.ቁ. 79/4)

 • የፀደቀ የፕሮጀክት ሰነድ ፕሮፖዛል
 • ከመንግስት መ/ቤት ጋር የተፈረመ የስምምነት ሰነድ
 • የታደሰ የማህበራት ምዝገባ ሠርተፍኬት
 • የዕቃ ማስጫኛ ሰነድ
 • ኢንቮይስ/ Invoice /
 • የዕቃ ማሸጊያ ዝርዝር/Paking List /
 • የስጦታ ምስክር ወረቀት/Donation certficate /
 • ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል የተፃፈ የትብብር ደብዳቤ
 • ድርጅቱ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር የተፈራረመዉ የአጠቃላይ አተገባበር ስምምነት ሰነድ (ለመጀመሪያ  ቀረጥና ታክስ ነፃ ጥያቄ ብቻ)::

ከቤተሰብ በአውሮፕላን የተላከልኝን ዕቃ መድረስ አለመድረሱን ማረጋገጥ የምችለዉ እንዴት ነዉ?

ከዉጭአገር የተላኩ ዕቃዎች በአየር ይሁን በየብስ ተጓጉዘዉ የተፈለጉበት ቦታ መድረስ አለመድረሳቸዉን ለማረጋገጥ የሚችሉትም ሆነ የሚረከቡት ከአጓጓዥ ድርጅቱ መሆኑ ይታወቃል፤ስለዚህ በአየር ተጓጉዞ የመጣን የግል ይሁን የንግድ እቃን መድረሱን ማረጋገጥ የሚቻለዉ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ነዉ፡፡

ከቀረጥ ነጻ ያስገባነዉ የኢንቨስትመት መኪና አስር አመት ስለሞላዉ መሸጥ ፈልገን ነበር ምን ማድረግ ይገባናል?

በቀረጥነፃ የገባን ተሸከርካሪ 10/አስር/ አመት ከሞላዉ በኋላ ወደ ሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ በሚፈለግበት ወቅት በመጀመሪያ ተሸከርካዉ በገባበት የጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ቀርቦ የ “0” ዜሮ ዲክለራሲዮን ማዉጣት ይጠበቅበታል፤ይህ ከሆነ በኋላ ንብረትነቱን ማስተላለፍ ይችላል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማራን ነን ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ፈልገን ነበር ምን አይነት ማበረታቻ አለን?

በኮንስትራክሽንየኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማራ ባለሃብት ለኢንቨስትመንት መስኩ የሚያስፈልጉትን የካፒታል እቃዎች በሙሉ ከቀረጥ ነፃ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ለዘርፉ የተሰጠዉን ማበረታቻ በተመለከተ የገቢ ግብር ዕፎይታ የሌለዉ ሲሆን የተሸከርካሪ ማበረታቻን በተመለከተ ደግሞ፤

ተራ ቁጥር

የኮንስትራክሽን ዘርፍ

ደረጃ

አንድ

ደረጃ 

ሁለት

ደረጃ

ሶስት

ደረጃ

አራት

ደረጃ

አምስት

 

 

  1

ጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት

 

 

 

 

 

1.1.      ፒካ አፕ

  2

  1

  1

  1

  1

1.2.      የጭነት መኪና

  -

  -

  -

  -

  -

1.3.      የዉሃ መያዣ የተገጠመለት መኪና

  1

  1

  -

  -

  -

1.4.      የዉሃ መርጫ የተገጠመለት መኪና

  1

  1

  -

  -

  -

 

  2

የሕንፃ ስራ ተቋራጭነት

 

 

 

 

 

2.1.   ፒካ አፕ

  2

  1

  1

  1

  1

2.2.   የጭነት መኪና

  -

  -

  -

  -

  -

2.3.   የዉሃ መያዣ የተገጠመለት መኪና

  2

  1

  -

  -

  -

 

  3

 

የመንገድ ስራ ተቋራጭነት

 

 

 

 

 

3.1.   ፒካ አፕ

  2

  1

  1

  1

  -

3.2.   የዉሃ መያዣ የተገጠመለት መኪና

  1

  1

  -

  -

  -

3.3.   የዉሃ መርጫ የተገጠመለት መኪና

  2

  1

  -

  -

  -

 

  4

 

 

ልዩ ሥራ ተቋራጭነት (ለኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ ብቻ)

 

 

 

 

 

4.1.  ፒካ አፕ

  1

  1

  -

  -

  -

4.2.  የጭነት መኪና

  -

  -

  -

  -

  -

 

 

  5

የዉኃ ሥራ ኮንስትራክሽን ተቋራጭነት

 

 

 

 

 

5.1.  የዉኃ ጉድጓድ ቁፋሩ

ለአንድ ድሪሊንግ  ሪግ 1 ፒክ አፕ ፤ 1 ክሬን ትራክና 1 የጭነት መኪና፤ ሆኖም የሚፈቀደዉ ፒክ አፕ ብዛት ከ4 መብለጥ የለበትም፡፡

5.2. ሌላ የዉኃ ሥራ ኮንስትራክሽን ተቋራጭነት

  2

  1

  -

  -

  -

  6

 የመሰረት ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ስራ ተቋራጭነት

ለአንድ መቆፈሪያ /መሰርሰሪያ መሣሪያ 1 ፒክ አፕ፤ 1 ክሬን ትራክ እና 1 የጭነት መኪና ፤ ሆኖም የሚፈቀደዉ ፒክ አፕ ብዛት ከ4 መብለጥ የለበትም፡፡

  7

የማእድን ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ስራ ተቋራጭነት

ለአንድ ድሪሊንግ  ሪግ 1 ፒክ አፕ ፤ 1 ክሬን ትራክና 1 የጭነት መኪና፤ ሆኖም የሚፈቀደዉ ፒክ አፕ ብዛት ከ4 መብለጥ የለበትም፡፡

(መ.ቁ. 4/2005 አንቀፅ6)

ባለአራት/4/ ኮከብ ሆቴል በመገንባት ላይ ነኝ ለሆቴሉ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት የምችለዉ ምንድን ነዉ?

ባለአራት/4/ ደረጃ ኮከብ ሆቴል ለመገንባት የሚያስፈልገዉ የግንባታ ዕቃ እና የካፒታል ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት ይቻላል ፤ የግንባታ ዕቃዉ መጠን በባለሙያ የተሰራ ቢል ኦፍ ኳንቲቲን መሰረት አድርጎ ሲሆን የካፒታል ዕቃዉን በተመለከተ ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ባወጣዉ መ.ቁ.5/2007መሰረት ይሆናል፡፡

የደረጃአምስት/5/ የግንባታስራተቋራጭ ኢንቨስትመንት ፍቃድ አለኝ፣ ምንአይነትተሸከርካሪከቀረጥ ነፃ ማስገባት ይፈቀድልኛል?

ደረጃ 5 የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ኢንቨስትመንትፈቃድ ላለው ግለሰብ/ድርጅት አንድ ፒክ አፕ ከቀረጥ ነፃ ማስመጣት ይፈቀዳል፡፡

ከቀረጥ ነጻ ያስገባናቸዉን መኪናዎች እና ማሽነሪዎችን ለሌላ ተመሳሳይ የቀረጥ ነጻ መብት ላለዉ ማዘዋወር ፈልገን ነበር ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?

የሚተላለፍለት ግለሰብ/ድርጅት የቀረጥ ነፃ መብት ያለው ስለመሆኑ በማረጋገጥ ዕቃው በገባበት ቅ/ጽ/ቤት በመሄድና ግብር ከሚከፈልበት ቅ/ፅ/ቤት ክሊራንስ በማቅረብና የገዢና ሻጭ ዉል ተፈፅሞ ለፈቃጁ አካል በማቅረብማስተላለፍ ይቻላል፡፡

ከቀረጥነጻያስገባናቸዉንመኪናዎች የቀረጥነጻመብትለሌለዉሰዉመሸጥፈልገን ነበርምንማድረግይጠበቅብናል?

ከቀረጥ ነፃ የገቡ ተሽከርካሪዎች የቀረጥ ነፃ መብት ለሌለው ግለሰብ/ድርጅት ለማስተላለፍ/ለመሸጥ የሚቻለው መጀመሪያ ቀረጥና ታክሱን ለሚመለከተው አካል በመክፈል መሸጥ ይቻላል፡፡

የኮከብ ደረጃ ያለዉ ሎጂ/ሆቴልግንባታለመገንባትፈልገንነበርየግንባታዕቃከቀረጥነጻማስገባትይፈቀድልናል?

የኮከብ ደረጃ ባለው ሆቴል/የሎጅ አገልግሎት የሚሠማራ ማንኛውም ባለሀብት ለሚያቋቁመው አዲስ  ወይም ነባሩን ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል የሚያስፈልጉ የካፒታልና የግንባታ ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማስገባት ይቻላል፡፡

ከቀረጥ ነጻ ያስገባናቸዉን ማሽነሪዎች በጊዜያዊነት ለስራ ወደዉጭ ሃገር ማስወጣት ፈልገን ነበር ይቻላል? ምን ማሟላት አለብን?

ማሽነሪዎች ለተለያዩ ምክንያቶች በጊዜያዊነት መውጣት የሚችሉ ሲሆን፣ በሚወጡበት ጊዜ የዕቃው ቀረጥና ታክስ ሊሸፍን በሚችል መጠን ዋስትና ማሲያዝ ያስፈልጋል፣ የወጡት ማሽነሪዎችኘሮጀክቱ እንደተጠናቀቀ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡

በትራንስፖርትዘርፍላይተሰማርተናልየፒክ አፕማበረታቻይፈቀድልናል?

የትራንስፖርት አገልግሎት የቀረጥ ነፃ መብት ከማይፈቀድባቸው የሥራ መስክ በመሆኑ አይፈቀድም፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ከቀረጥ ነጻ ሊፈቀዱ የሚችሉት የካፒታል ዕቃዎች ምን ምን ናቸዉ?

ለኮንስትራክሽን(የስራ ተቋራጭ ኢንቨስትመንት)የካፒታል ዕቃዎች የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዉን ለመስራትና የስራ ደረጃዉን ለመስጠት እንዲሟሉ የጠየቃቸዉ ዕቃዎች ይሆናሉ::

ከቀረጥ ነጻ ያስገባነዉን መኪና በባንክ አስይዘን መበደር እንችላለን ወይ? የምንችል ከሆነ መከተል ያለብን ቅድመ-ሁኔታዎች ምን ምን ናቸዉ? አዎ ይቻላል::

 • ከገቢ ባለስልጣኑ ጋር በቀረ­ጥና ታክሱ አከፋፈል ላይ ስምምነት ማድረግ
 • የዕቃዉን ቀረጥና ታክስ መጠን ማስላትና ለባንኩ ማቅረብ
 • የቀረበለትን የቀረጥና ታክስ መጠን ለባለስልጣኑ ለመክፈል ባንኩ የተስማማ መሆኑን የሚያረጋግጥ የስምምነት መግለጫ

አካልጉዳተኞች ነን መኪና ከቀረጥ ነጻ ማስገባት እንችላለን ወይ?

አዎ ይቻላል

 • አንድ ባለሁለት ወይም ባለሶስት እግር ወንበር ባለሞተር ተሽከርካሪ
 • አንድ ከ1600 ሲሲ ያልበለጠ ልዩ አዉቶሞቢል::

ከቀረጥ ነጻ ላስገባናቸዉ ማሽኖች መለዋወጫዎችን ከዉጭ ለማስገባት ምን ማሟላት አለብን?

 • ዕቃዎች የገቡት በኢንቨስትመንት ፈቃድ ከቀረጥ ነፃ መሆን አለባቸዉ::
 • ለአንድ ጊዜ ብቻ  ማሽኖች ወደ ሀገር ከገቡበት ቀን ጀምሮ በአምስት አመት ጊዜ ዉስጥ ማሰገባት::
 • የግዥዉን መጠን መሰረት ያደረገ መለዋወጫ 15 በመቶ በማስላት ለጉምሩክ ማቅረብ::

የኢንቨስትመንት ፈቃድ አዉጥተን የህዝብ ት/ቤት አቋቁመናል ለተማሪዎች ሰርቪስ ከቀረጥ ነጻ ከዉጭ ማስገባት ይፈቀድልናል

አይፈቀድም::

ዲያስፖራ ነኝ በሪል-ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርቻለሁ የግንባታ ዕቃዎችን በፍራንኮ ቫሉታ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት እችላለሁ?

ለሪል-ስቴት ኢንቨስትመንት የግንባታ ዕቃ በፍራንኮ ቫሉታም ሆነ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት   አልተፈቀደም ::

ለኤንጂኦ/NGO/ ተሸከርካሪ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ፈልገን ነበር ምን ምን ቅድመ-ሁኔታዎችን ማሟላት አለብን?

በፌደራልመንግስት ወይም በክልል መስተዳድር መስሪያ ቤት የፀደቀ፤ስምምነት የተደረሰበት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ከመንግስት መስሪያ ቤት ጋር የተፈረመ የስምምነት ሰነድ ያለውና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለሚካሄድ ለማንኛውም ፕሮጀክት ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ እንዲገባ የሚፈቀደው ተሸከርካሪ ዓይነት ፎር ዊል ድራይቭ ፒክ-አፕ ወይም ስቴሽን ዋገን ሆኖ የሚፈቀደው የተሸከርካሪ ብዛት በዋጋ ከፕሮጀክቱ ካፒትል 10% (አስር በመቶ) ሳይበልጥ ሁለት ብቻ ይሆናል፡፡

የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራዮች ነን የመኪና ማበረታቻ ይፈቀድልናል?

ለኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራዮች የተሸከርካሪ ማበረታቻ አይፈቀድም፡፡ ገልባጭ እንደ ልማት ዕቃዎችና መሳሪያዎች የሚቆጠር በመሆኑ እንደ ተሸከርካሪ አይታይም፡፡

በአስጎብኝነት የስራ መስክ የተሰማራሁ ባላሀብት ነኝ ከቀረጥ ነጸ ያስገባኋቸዉን ተሸከርካሪዎች ስራ በማይኖረኝ ወቅት /በማልጠቀምበት ወቅት/ ተገቢዉን ግብር እየከፈልኩ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ማከራየት እችላለሁ?

ተገቢውንግብር በቅድሚያ ከፍለው ማከራየት ይችላሉ፡፡

በኮንስትራክሽን መስክ የተሰማራሁ ስራ ተቋራጭ ነኝ ከቀረጥ ነጻ ያስገባኋቸዉን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በማልጠቀምበት ወቅት ተገቢዉን ግብር እየከፈልኩ ለሌሎች ማከራየት እችላለሁ?

ተገቢውንግብር በቅድሚያ ከፍለው ማከራየት ይችላሉ፡፡

ለጉምሩክ ጉዳይ የቤተሰብ ትርጉም ወንድምና እህትን ይጨምራል?

የቤተሰብትርጉም ወንድምና እህትን አይጨምርም፡፡

ደረጃ 6 እና ከ6 በታች (ደረጃ 7,8,9,10…) የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ የኢንቨስትመንት ፈቃድያለን ባለሀብቶች ለስራችን የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን ከቀረጥ ነጻ ማስገባት እንችላለን? ፒካፕ ተሸከርካሪስ ከቀረጥ ነጻ ማስገባት እንችላለን?

ፒካፕ ተሽከርካሪ የማይፈቀድ ሲሆን ለደረጃው ያስፈልጋሉ ተብለው በከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጡት የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ከቀረጥ ነፃ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡

end faq

የተፋጠነ የቀረጥ ተመላሽ ስርዓት ምን ማለት ነው?

በወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 768/2004 ድንጋጌ መነሻነት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ያወጣውን የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 35/2005 መሰረት አድርጎ የሚፈፀም በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በወጪ ንግድ ስራ ላይ የሚሰማሩ ባለሃብቶች የሚበረታቱበት ስርዓት ነው፡፡ በዚህም መመሪያ የተፋጠነ ቀረጥ ተመላሽ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ ላኪዎች ያመረቱት ሸቀጥ ወደ ውጭ መላኩን መጠበቅ ሳያስፈልግ ለውጭ ገበያ ለሚያቀርቡት ሸቀጥ ማምረቻ እንዲውል በአገር ውስጥ በፈጸሙት የግብዓት ግዥ ላይ ወይም ለውጭ ገበያ ለሚቀርቡት ሸቀጥ ማምረቻ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማምረት በአገር ውስጥ በፈፀሙት የግብዓት ግዥ ላይ የከፈሉት ቀረጥ የአገልግሎት ጥያቄው በቀረበ ቢበዛ በ7 ቀን ጊዜ ውስጥ ባለስልጣኑ የተከፈለውን የቀረጥ ሂሳብ ለአመልካቹ ተመላሽ የሚደረግበት ስርጫት ነው፡፡

 

የተፋጠነ የቀረጥ ተመላሽ ስራዓት መመሪያ አጠቃላይ ይዘት ምንን ያካተተ ነው?

መመሪያው የተፋጠነ የቀረጥ ተመላሽ ስርዓት ተጠቃሚዎ ሊያሟሏቸው የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች፣ የተጠቃሚዎችን አመራረጥ፣ ከተስተናገዱ በኋላ እሰከ ሪፖርት አቀራረብ ድረስ ያለውን የክትትል ስርዓት እንዲሁም በላኪዎች፣ በባለስልጣኑ መ/ቤት እና በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መከናወን ስለሚገባቸው ዝርዝር ተግባራት የያዘ ለአፈፃፀም ቀላልና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ከመጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ ያለ መመሪያ ነው፡፡

የተፋጠነ ተመላሽ ስርዓት ተጠቃሞዎች የሚለዩት ወይም የሚመረጡት በማን ነው?

የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሚለዩት መስፈርት በወጪ መስፈርት በወጪ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩና ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኙትን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ አምራች ላኪዎችን ሲሆን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ መስፈርቱን የሚያሟሉትን በመምረጥ በየጊዜው ዝርዝራቸውን ለአፈፃፀም ወደ ባለስልጣን መ/ቤቱ እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ተብለው የተለዩት እስከ አሁን ያለው አፈፃፀማቸው ምን ይመስላል?

በተለያየ ጊዜ እስከ አሁን የስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ 36 ግብር ከፋዮች ቢሆኑም ባለን መረጃ በስርዓቱ እየተጠቀሙ ያሉት 12 የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ብቻ ናቸው፡፡ ይህም የወጪ ንግዱን ለማበረታታት በመንግስት ታምኖበት የተዘረጋው ይህ ስርዓት የታለመለትን ዓላማ እያሳካ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ልዩ ትኩረት የተሰጠውን የወጪ ንግድ ለመደገፍ በስርዓቱ ምንነትና ጠቀሜታ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ መፈጠር ይኖርበታል፡፡ ግብር ከፋዮች የተለየ መብት በሚሰጠው በዚህ ስርዓ በመታቀፍ  ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥያቄያቸውን ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ማቅረብ፤ የተመረጡትም የሚፈለግባቸውን አሟልተው ቴያቄያቸውን ለባለስልጣኑ በማቅረብ በስርዓቱ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡

የተፋጠነ ተመላሽ ስርኣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ ላኪዎች በተፈቀደላቸው መሰረት ለመጠቀም ምን ይጠበቅባቸወል? ያለባቸው ግዴታስ?

በተለያየ ጊዜ እስከ አሁን የስራዓቱ ተጠቃ እንዲሆኑ የተመረጡ 36 ግብር ከፋዮች ለዚሁ ዓላማ ባለስልጣኑ ያዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት ለውጭ ገበያ ለሚያቀርቡት ሸቀጥ ማምረቻ እንዲውል በአገር ውስጥ በፈፀሙት የግብአት ግዥ ለሚያቀርቡት ሸቀጥ ማምረቻ እንዲውል በአገር ውስጥ በፈፀሙት የግብአት ግዥ ላይ ወይም ለውጭ ገበያ ለሚቀርብ ሸቀጥ ማምረቻ የሚያስፈልገውን ግብአት ለማምረት በአገር ውስጥ በፈፀሙት የግብአት ግዥ ላይ የከፈሉት ቀረጥ ተመላሽ እንዲደረግላቸው ክፍያ ከፈጸሙት እና ተያያዥ ማስረጃ ጋር በየወሩ በግብር ከፋይነት ለተመዘገቡበት ቅ/ጽ.ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ያለአግባብ ተመላሽ የተደረገው የቀረጥ ሂሳብ መኖሩ ሲረጋገጥ ምን ይደረጋል?

የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በተቀመጠው ጊዜ ሪፖርት የማያቀርቡ ወይም የቀረበው ሪፖርት በአገር ውስጥ በገዙት ግብአት ተጠቅመው ያመረቱትን ምርት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ወደ ውጭ መላኩን ወይም ለቀጥተኛ አምራች ላኪ በግብአትነት መቅረቡን የማያረጋግጥ ከሆነ ባለስልጣኑ ለውጭ ገበያ ባልዋለው ወይም ለቀጥተኛ አምራች ላኪ በግብአትነት ባልቀረበው መጠን ተመላሽ የተደረገውን ሂሳብ እንዲከፈል የማድረግ የገቡበትን ግዴታ ያልተወጡ ተጠቃሚዎች በወንጀል ኃላፊነት ተጠያቂ ይደረጋሉ፡፡ ከስርዓቱ ተጠቃሚዎች ዝርዝር እንዲወጡና የተሰጣቸው መብት ይቋረጣል፡፡

የተፋጠነ ተመላሽ ስርዓት ከማበረታታትና ከመደገፍ ጎን ለጎን የክትትልና ቁጥጥር ስራው ምን ይመስላል?

ባለስልጣኑ የተጠቃሚዎቹ የንግድ ስራ እንቅስቃሴ እና ከንግድ ስራው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በመርመር የሚቀርቡ ሪፖርቶች ትክክለኛነት በኦዲት ይረጋገጣል፡፡

በፈጣን ተመላሽ የሚስተናገዱ ግብር ከፋዮች ዝርዝር

ተ.ቁ

የድርጅቱ ስም

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

የተሰማራበት ዘርፍ

የሚስተናገድበት ቅ/ጽ/ቤት

የተፈቀደላቸው የፈጣን ተመላሽ እድል እየተጠቀሙ ያሉ ግብር ከፋዮች

1

Ziway Rosses Pls

0002504886

አበባ

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

2

ጆይ ቴክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000610750

አበባ

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

3

ኤ.ኪው ሮዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0002662969

አበባ

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

4

አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000044654

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

መቀሌ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

5

ሼባ ቆዳ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000044562

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

መቀሌ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

6

ሳይገን ዲማ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

0004995829

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

7

ሆራ ቆዳ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000109562

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

8

ብራም ፍላዎርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0005150757

አበባ

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

9

ኽረርግ ፍላዎርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0003067301

አበባ

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

10

ኮልባ ማልፊያና መለስለሻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000960026

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

11

ሞጆ ቆዳ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000050211

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

12

የኢትዮጵያ ቆዳ አክሲዮን ማህበር

0000109613

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

አዳማ ቅ/ጽ/ቤት

እየተስተናገደ ያለ

13

ድሬ ኢንድስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000007324

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

14

ካንጋሮ ጫማ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000010388

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

15

ዋልያ ቆዳ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000011925

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

16

አንበሳ ጫማ አክሲዮን ማህበር

0000015839

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

17

ወይኑ ካርቴን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000037159

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

18

ባቱ የቆዳ ማልፊያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000042807

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

19

ጄንዩን ሌዘር ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000044866

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ምዕራብ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

20

ኒት ቱ ፋኒሽ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000959963

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

21

ኖቫስታር ጋርመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0001750431

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

22

ሙያ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0001868496

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምዕራብ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

23

ገላን ቆዳ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0001218624

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

24

ኤክስፔሪያንስ ኢንኮርፖሪቲድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0001228626

Scientific and technical consulting service

ምዕራብ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

25

ጥቁር አባይ ጫማ አክሲዮን ማህበር

0000007485

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

26

ኢትዮ ሌዘር ኢንድስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር()

0000017382

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

27

አጊስታ(አዲስ ጋርመንት) አክሲዮን ማህበር

0000015696

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምዕራብ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

28

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

0000020351

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት

 

29

ክራውን ቴክስታይል ዊቪነግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0001645755

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

30

አዳማ ስፕሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0003003849

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

31

ቦስቴክስ ጫማ ፋብሪካ

0002247605

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ምዕራብ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

32

ሐፋድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000022594

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

33

ከቢር ኃ/የተ/የግ/ማህበር(ጋርመንት)

0000344132

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

34

ቪትኮን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0002242736

ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

35

እልፍነሽ ዘላለም ጫማ እና ቆዳ (ራምሴ ጫማ ፋብሪካ)

0000041099

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

36

ብሉ ናይል ቆዳ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

0000009490

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች

ምስራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

 

end faq

What is VAT?

VAT (Value Added tax) is a tax on consumption. It is charged on most goods and services which are purchased by an individual and enterprises.

How does VAT work?

VAT is essentially charged on the difference between the sale prices of the good or service provided (outputs) and the cost of goods or services (inputs) bought for use in the production of goods or services at each stage of the production /distribution process.

 

Who collects VAT?

VAT is collected on behalf of Ethiopian Revenues and customs Authority (ERCA) by individuals firms and organizations that carry out taxable supplies

 

Who is taxable person?

A taxable person is an individual, business enterprise or organization who independently carries out an economic activity. Any individual business or organization that is registered or is required to be registered, a person carrying out taxable import of goods to Ethiopia and a non-resident person who performs services without registration for VAT are subject to taxation.

 

What is taxable activity?

The activity which is carried on continuously or regularly by any registered person in Ethiopia or party in Ethiopia Whether or not carried on continuously or regularly for a pecuniary profit that involves or is intended to involve, in the whole or in part, the supply of goods or services to another person for consideration.

 

What are Exempted Transactions from VAT?

 1. "Dwelling" means any building, premises, structure
 2. The sale or transfer of a used dwelling, or the lease of dwelling.
 3. The rendering or financial services.
 4. The import of goods to be transferred to the National Bank of Ethiopia
 5. The rendering by religious organizations of religious or church related services.
 6. Rendering of medical services
 7. Rendering of educational services
 8. The supply of electricity & water and so on are among the many.

 

What is the supply of goods or supply of services mean?

A supply of goods or a grant of the use or right to use goods under a rental agreement, credit agreement, freight contract, agreement for charter, or any other agreement under which such use or right to use is granted, including provision of thermal electrical energy gas or water.

 

What are taxable supplies?

These are goods and services other than those classified exempt supplies. Certain supplies are exempt from VAT for example

 

What is taxable importation?

Taxable importation is the importation of any good in to Ethiopia, with the exception of certain goods which have been classified as exempt importation, are subject to 15% taxation.

 

What must you do as a taxable person?

If you are a taxable person you must, by law fulfill the following obligations

 

end faq

What is Employment Income Tax?

Employment income tax is a tax on the earnings of an employee. The government collects this tax from any individual employees, other than contractors, engaged whether on a permanent or temporary basis to perform services under the direction and control of the employer. Employment income includes any payment or gain in cash or in kind received from employment by the employee subject to certain exemptions: see below. Employment income is one of the most well known forms of tax in Ethiopia. In 2008/9 fiscal year, employment income tax amounting to 1.017 billion birr was collected from payments made by employers to employees. This represents 4.31% of the total revenue collected by the Tax Authority in that fiscal year.

 

end faq

What is customs examination of goods?

To speed up the examination of the goods, the customs officer uses scanning machines which takes approximately three to five minutes. This has enabled ERCA to detect a wide variety of illegal goods concealed in the import-export cargo. The examination is directed against smuggling, an illegal act of bringing or taking out of the country goods for which duty has not been paid and goods the importation or exportation of which is prohibited. The examination of import export goods is under the jurisdiction of customs stations, branch offices of the Ethiopian Revenues and Customs Authority (ERCA).

 

Which goods are to be examined by scanning machine?

All import-export and transit goods which its risk level is red are to be examined by scanning machine. The examination of the goods takes place at the entry or exit customs control stations at the border and at any place in the transit route where scanning machine is installed.

 

What if your cargo is suspected of smuggled goods?

When the result of the scanning machine leads to a suspicion that there might be smuggled goods in your cargo, the customs control station may escort the suspected cargo to its destination. Then, the customs station at the destination examines the goods manually, studies the nature of the violation against customs law and its negative impact on the interest of the government and the public at large. Finally, resolves the offence using a method which has two aspects. First, the customs station tries to solve the problem administratively if it believed that the offence involved with smuggling is only a minor one. Second, if the customs station believed that the smuggler has committed serious offence, the case will be taken to court.

 

Is there any service charge for goods examined by scanning machine?

All goods examined by scanning machine shall pay service charge of 0.07 percent of the duty paying value of the goods. However, the following goods are excluded from service charge:

 1. goods entitled to be beneficiary of export trade incentive scheme
 2. export goods
 3. goods imported by embassies, continental and international organizations
 4. goods imported by government organizations

 

end faq

How can I calculate the total payable tax on my imported item?

What do we mean by Hs Code, Cost, Insurance, and Freight? HS Code is a standardized multi-functional system to classify goods, universally applied by government of all countries, international organizations and individuals in many other fields, such as domestic tax, trade policy, price control, quota control, budgeting, economic research and analysis. Therefore HS Code becomes a universally recognized classification standard and economic language. For instance the Hs Code of offset printing machinery, sheet fed, and office type is 84431200. The HS Code of any specific product has eight digits. You can make a rough calculation of the likely payable tax on your imported item using the tax calculator in the left column of our website. The calculator operates if only it is fed with the correct information. Some of the information the calculator needs include Hs Code, Cost, Insurance, Freight and other costs of your imported item.

Cost

Insurance represents the money or premium that is paid to deliver the item to be imported up to a prescribed customs port. Freight is money paid for the commercial means of transport for delivering the imported item up to the first customs port. Cost stands for the transaction value and other related costs or payment made in exchange for the purchase of your item. Insurance represents the money or premium that is paid to deliver the item to be imported up to a prescribed customs port. Freight is money paid for the commercial means of transport for delivering the imported item up to the first customs port.

 

Exemplary way to calculate customs duty and other taxes on printing machinery

The first step is to click on the Tax Calculation folder. The click on this folder provides you a tax calculator form. In this form you are required to fill the foregoing Hs Code, Cost, insurance, freight and other costs of the imported item. When you completed the form, click on 'Calculate Tax'. The click gives you the rough total payable tax of 1559.55 birr, CIF value (Cost +Insurance +Freight) of 3700 birr and other information about the type of taxes and rates applied to your imported item. In case the HS Code is unknown to you, then you have to click on 'Search on Hs Code' in the left column of our web and this provides a pattern which has three boxes, including Search Option box, HS Code box and Find box. The first box contains an arrow. The click on the arrow provides you two options. These options are 'HS Code' and 'Goods Description'. Then select to use 'goods description' and fill the nomenclature (specific name of your imported item indicated in the Harmonized Commodity Description and Coding System, HS) in the 'Goods Description'box. For instance if the specific name of your imported item is 'Printing Machinery', Let's consider a specific example: you have imported printing machinery into Ethiopia. Hs Code of your printing machinery is 84431200. Suppose, its cost is 3000 birr, payments to insurance and freight companies are respectively 300 birr and 400 birr, and other costs nil (0), how do you think the total customs duty and other taxes can be calculated?

 

Hs Codes

Recommendation The calculator produces erroneous information if your input is incorrect. For instance, if you put into the 'Goods Description' box the word 'Printer' or the phrase 'Printing Machine' instead of 'Printing Machinery' it would not be likely for you to get the desired result. To avoid erroneous results, it is advisable to use those names of the imported item which is indicated in the HS Code. You fill this name in the foregoing box and click on 'find' This provides you a list of 'HS Codes' and 'Goods Description' Out of the list, you have to select the Hs Code and Goods Description that best suits your imported item. Once you select the Hs Code of your imported item, the next step is to fill it in the 'Tax Calculation' form and click on 'Calculate Tax'.

end faq

Add comment

We want to hear from you and strive to make our Website better and user friendly.

Please don't ask Questions here bcz there is a forum link for questions and answers since you may not get an answer from Feedback.


Security code
Refresh

Comments  

#70 WebAdmin 2017-08-04 12:53
Quoting ABDULAZIZ:
I HANDICAPPED LIVE IN OUT SIDE MORE THAN ARROUND 20 YEARS NOW DEPEND ON ON NEW POLICY FREE TAX CAR FOR HANDICAPPED PERSON I NEED TO KNOW WHATS THE CONDITION FOR DIASPORA HANDICAPPED PERSON

አካል ጉዳተኞች የግል አገልግሎት የሚውል ተሸከርካሪ ከቀረጥ ነፃ የሚያስገቡበትን ሁኔታ ለመወሰን በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር በወጣው መመሪያ ቁጥር 41/2007 አንቀፅ 6(2) መሰረት የሌላ አገር ዜጋ የሆነ ትውልድ ኢትዮጵያዊ አካል ጉዳተኛ በቋሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ወደ አገር ጠቅልሎ መግባቱን፣ ይኖርበት ከነበረው አገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ የተሰጠ ማስረጃ ሲያቀርብ እና ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ከሚኖርበት የአካባቢ አስተዳደሪ በቋሚነት ቢያንስ አንድ አመት የኖረ ስለመሆነ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ሲያቀርብ እና በዚህ መመሪያ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ አንድ ተሸከርካሪ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ሊፈቀድ ይችላል፡፡
41/2007 link : www.erca.gov.et/images/Documents/Disability.pdf
Quote
-1 #69 WebAdmin 2017-07-24 15:26
Quoting Alemeshet Lemma:
Greetings,
I am Alemeshet Lemma (Ethiopian) and I have been working in Uganda for the last two years. I wanted to buy a minibus for public transport so that I support my family and myself when I am back. I don't have much money to buy it locally as cars are very expensive there.
1. Am I allowed to import a car (Van) for public transport use?
2. What will be the total tax that I have to pay?
3. What documents and prerequisites do I need to import a car?
4. How long does it take to finish the whole process of paying the taxes and clearing the vehicle from the customs?
5. ...

አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ ሀገር ቆይተው ጠቅልለው ለሚመለሱ ኢትዮጵውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንድ የግል አውቶሞቢል ቀረጥና ታክስ በመክፈል ማስገባት ይችላሉ ነገር ግን ለንግድ አላማ የሚውል ማንኛውም ተሽከርካሪም ሆነ ዕቃ አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ቢቆዩም ከውጭ ይዘው መምጣት አይችሉም፡፡ እርሶ በኡጋንዳ የቆዩት ሁለት ዓመት ብቻ ስለሆነ ማናቸውንም አይነት ተሽከርካሪ ማስገባት የማይችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Quote
-1 #68 WebAdmin 2017-07-24 15:04
Quoting DANIEL AELMU:
በፌ.ታክስ አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሰረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ተቀንሶ ለባለስልጣኑ ማስተላለፍ ያለበት ማንኛዉም ሰዉ ሳይቀንስ የቀረ ወይም ቀንሶ ለባለስልጣኑ ያላስተላለፈ መቀጫ እንዲጣልበት ተደንግጓል ይህ ቅጣት በመመሪያ 55/03 መሰረት በከፊል ይነሰል?

የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/08 ማንኛውም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ገቢ የማድረግ ግዴታ የተጣለበት ግብር ከፋይ ግብር ቀንሶ ያላስቀረ እንዲሁም ቀንሶ ያስቀረውን የገንዘብ መጠን ለባለስልጣኑ ያላሳወቀ እንደሆነ ተጠያቂ እንደሚሆን እና ቅጥት እንደሚጣልበት ይደነግጋል፡፡ ይህን ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ባለመቀነስና ባለማሳወቅ የሚጣል መቀጫ በመመሪያ ቁጥር 55/03 አንቀጽ 9 ተራ ቁጥር 3 እና 4 መሰረት የማይነሳ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Quote
+1 #67 WebAdmin 2017-07-24 14:55
Quoting Alemberhan Abraha:
Dear Sir/Madam
Would you please send me how severance pay and compensation income tax is calculated including the manuals.
Thanks,
Alemberhan

የሴቨራንስ ፔይመንት ክፍያ ግብር አሰላልን በተመለከተ መጀመሪያ ተቀጣሪው የተሰጠውን (የወሰደውን) የገንዘብ መጠን ግለሰቡ ተቀጣሪ በነበረበት ወቅት ይወስደው ለነበረው የመጨረሻ ወር ደመወዝ በማካፈል የወሰደውን የገንዘብ መጠን የስንት ወር ደመወዝ እንደሚሸፍን በማወቅና በመጨረሻ ወር ደመወዙ የከፈለውን የስራ ግብር ከላይ በስሌት በተገኘው ቁጥር በማባዛት ተከፋይ የስራ ግብር ማግኘት ይቻላል፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ 979/08 አንቀጽ 65/1/ሀ መሰረት በተቀባይ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ምክንያት የሚከፈል ካሳ ከገቢ ግብር ነፃ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ይህን የሚያብራራ ዶክመንት በኢሜል አድራሻዎ አታች አድርገንሎታል፡፡ ስለጠየቁን እናመሰግናለን!
Quote
#66 ABDULAZIZ 2017-07-12 06:40
I HANDICAPPED LIVE IN OUT SIDE MORE THAN ARROUND 20 YEARS NOW DEPEND ON ON NEW POLICY FREE TAX CAR FOR HANDICAPPED PERSON I NEED TO KNOW WHATS THE CONDITION FOR DIASPORA HANDICAPPED PERSON
Quote
#65 shimelis 2017-06-28 19:17
ከኮንስትራክሽን ስራ ላይ የሚሰበሰብ መያዣ/retention money/ Vat ቅድሚያ እንደሚሠበሰብ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መመርያ/ ደንብ/ ደብዳቤ ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ብጠቁሙኝ?
Quote
#64 Mihiret Eskeziya 2017-06-23 07:12
I am very very satisfied with your Information, so keep up it :sigh:
Quote
#63 Alemberhan Abraha 2017-06-16 23:49
Dear Sir/Madam
Would you please send me how severance pay and compensation income tax is calculated including the manuals.
Thanks,
Alemberhan
Quote
+1 #62 DANIEL AELMU 2017-06-15 00:10
በፌ.ታክስ አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሰረት ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ታክስ ተቀንሶ ለባለስልጣኑ ማስተላለፍ ያለበት ማንኛዉም ሰዉ ሳይቀንስ የቀረ ወይም ቀንሶ ለባለስልጣኑ ያላስተላለፈ መቀጫ እንዲጣልበት ተደንግጓል ይህ ቅጣት በመመሪያ 55/03 መሰረት በከፊል ይነሰል?
Quote
#61 Alemeshet Lemma 2017-06-13 11:52
Greetings,

I am Alemeshet Lemma (Ethiopian) and I have been working in Uganda for the last two years. I want to come and work in my country since I am done living away from home and family. I wanted to buy a minibus for public transport so that I support my family and myself when I am back. I don't have much money to buy it locally as cars are very expensive there. I have the following questions.

1. Am I allowed to import a car (Van) for public transport use?
2. What will be the total tax that I have to pay?
3. What documents and prerequisites do I need to import a car?
4. How long does it take to finish the whole process of paying the taxes and clearing the vehicle from the customs?
5. Is there any special arrangement like paying the taxes in installments in a certain period of time or it is a must to pay it at once?
Your explanation will help me a lot and I thank you for your time
Quote
Visitors: Yesterday 6 | This week 1 | This month 2203 | Total 824986

We have 359 guests and no members online