ግብሩን ለማዘመን

Posted in Know How

የሃገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት በሚፈለገው መልኩ እንዲድግ ኢኮኖሚ ዕድገቱን የሚያግዝ ቀልጣፋ ግብር ስርኣት መዘርጋት እንዳለበት እሙን ነው፡፡ የግብር አሰባሰባችን እና አከፋፈሉ ስርዓት ፍትሃዊነት ያለው እንዲሆን እና ግብር የማይከፈልባቸው ገቢዎች በግብር መረብ እንዲገቡ ማድረግም አስፈላጊ ነው፡፡

በፊደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 ዓ.ም. በተደነገገው መሰረት ግብር ከፋይ ደረጃዎች ሦስት ናቸው፡፡ ደረጃ ‹‹ሀ››፣ ‹‹ለ›› እና ‹‹ሐ›› በመባል ይጠራሉ፡፡

ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢው ብር 1 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ድርጅት ወይም ማንኛውም ሌላ ሰው ደረጃ ‹‹ሀ›› ግብር ከፋይ በመሆን ይመደባል፡፡

እነዚህ ግብር ከፋዮች አመታዊ የግብር ማስታወቂ ጊዚያቸው ከሀምሌ1 እስከ ጥቅምት 30 ነው፡፡

የደረጃ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች የሚባሉት ድርጅቶችን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር 1 ሚሊየን በታች ነገር ግን ከ5መቶ ሺ በላይ የሆኑ ናቸው፡፡ ግብር የመክፈያ ጊዜያቸውም ከሃምሌ 1 እስከ ጷጉሜ መጨረሻ ነው፡፡

ከሃምሌ 1 እስከ ሃምሌ 30 ግብራቸውን የሚያሳውቁት ደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ድርጅቶችን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢያቸው ከብር 5መቶ ሺ በታች የሆኑ ናቸው፡፡

ይህ አመዳደብ በአመታዊ ጠቅላላ የገቢ እና በህግ ሠውነት ባለቸው ድርጅቶች የኢኮኖሚ መጠን ላይ በመመስረት የተሰራ ነው፡፡

በዚህም መሰረት የንግድ ስራ ግብር የመክፈል ኃላፊተት ያለባቸው የደረጃ‹‹ሀ›› ግብር ከፋዮች፤ በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሰረት የተዘጋጁ የሂሳብ መዝገቦችን የመያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡ ስለዚህ ግብር ከፋዩ ከሰራው ጋር በተያያዘ የንግድ ዕቃዎችን ግዚና ሽያጭ፣ የሀብት እና ዕዳዎች መግለጫ እንዲሁም በግብር ከፋዩ የተሰጡ እና የተገኙ አገልግሎቶችን በተመለከተ በዝርዝር መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

በእያንዳንዱ የግብር ዓመት የሚሰበሰበው ግብር እየጨመረ ቢመጣም መሰብሰብ ከሚገባው አንፃር እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ወጥነት ያለው እና ቀልጣፋ አሰራር አለመዘርጃቱ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት መንሰራፋቱ እንዲሁም በሃቅና በዕውነታ ላይ የተመሰረተ ግብር ከፋይ ያለመኖሩ ነው፡፡

ለእያንዳንዱ ሽያጭ ደረሰኞችን በመቁረጥ እና አገልግሎቱን በታማኝነት በመፈፀም የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ ግብር አሰባሰብ እንዲኖረን የሁላችንንም ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ምንም እንኳን በተፈለገው መልኩአገልግሎት አሰጣጡ የተቀላጠፈ እና የዘመነ ባይሆንም የሚታዩ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ወደተሸለ የግብር ስርዓት ማምጠት ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

Visitors: Yesterday 146 | This week 520 | This month 1516 | Total 435889

We have 462 guests and no members online