የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አርማ (logo) መግለጫ

Posted in Know How

የአርማው/ሎጎው ዋና ዓላማ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ አላማ፣ ስልጣንና ተግባር መሠረታዊ  ሃሳቦችን  ህብረተሰቡ  በአጭሩ  በምስል  እንዲረዳው  ማስቻል  ነው፡፡

የሚሽከረከሩ ቀስቶች

በአርማው ላይ የሚሽከረከሩ ሦስት ቀስቶች አምስት መሰረታዊ ጉዳዮችን  ያመለክታሉ፡፡

ተቋሙሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ለውጥ/Institutional transformation/ ለማምጣት በማያቋርጥ የለውጥ ኡደት/ሂደት ላይ መሆኑን

በተሰበሰበገቢ ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው ልማት በማረጋገጥ እና የድህነት ቀለበትን በመስበር አስተማማኝ ሰላምንና ብልፅግናን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት፣

የንግድና የኢንቨስትመንት ፋሲሊቴሽንን፣ የታክስና የጉምሩክ ህጎች ማስከበርን እና የገቢ አሰባሰብን

በሂደታዊ አደረጃጀት እራሱን ለመቆጣጠር በሚያስችል መንገድ የተዋቀየሥራዎችዘርውህድ መሆኑንና ዘርፎችም እርስ በርሳቸው የሚደጋጋፉ እና ተያያዥ መሆናቸውን፣

ቀስቶቹ የሚሽከረከሩበት ሰማያዊው መደብ የለውጥ ሞደናይዜሽንሥራዎች ዘርፍን፣ አረንዴው ቀስት የኮርፖሬት ስራዎች ዘርፍን፣ ቢጫው ቀስት የኦፕሬሽን ዘርፍንና ቀዩ ቀስት የህግ ማስከበር ዘርፍን ይገልፃሉ፡፡

ሚዛን

በአርማው ላይ የተመለከተው ሚዛን ሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች ይገልፃል፡፡

የዘርፉን ፖሊሲዎች፣ አዋጆችና ደንቦች በእኩልነት እና ፍትሃዊነት የሚተገበሩ መሆኑን እና በግብርና ቀረጥ ከፋዮች መካከል  አድሎ ሳይደረግ ከሙስና የፀዳ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን፣

ተመሳሳይ ገቢ ያላቸው ግብር ከፋዮች አንድ ዓይነት ታክስ ይጣልባቸዋል የሚለውን የታክስ አግድሞሽ እኩልነት (horizontal equity) እና የተሻለ ግብር የመክፈል አቅም ያላቸው ግብር ከፋዮች በተነፃፃሪ ከፍተኛ ታክስ ይከፍላሉ የሚለውን አምዳዊ የታክስ እኩልነት (Vertical equity) እና

የሰራተኞች ቅጥር፣ ዕድገት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ የስራ አፈፃፀም ምዘና እና ስንብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ፣ ደንብ እና በባለሥልጣየሰራተኞች አስተዳደር ደንብና የሥነ-ምግባር ደንብ መሠረት የሚከናወን መሆኑን ያመለክታል፡፡

የእጅ ለእጅ ትስስር

የእጅ ለእጅ ትስስሩ አራት አበይት ጉዳዮችን ያመለክታል፡፡

መንግሥትና ህዝቡ የገቢ ለልማት መርህን እውን ለማድረግ ቃል የገቡ መሆኑንና ለተቀናጀ ልማት የሚደረገውን የጋራ ጥረት፣ ትብብር እና ድጋፍ፣

የግብር ሰብሳቢውና የግብር ከፋዩ ግንኙነት በፈቃደኝነት የግብር አከፋፈል ስርዓት (Voluntary compliance) ላይ የተመሰረተ መሆኑን

የባለሥልጣሰራተኞች የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ቃል የገቡ መሆኑን

የሴት እና የወንድ እጅ፣ ሴቶች በአገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የጾታ እኩልነት ያመለክታል፡፡

የብርሐን ጨረር

በአርማው ላይ የተመለከተው የብርሃን ጨረር ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን ይገልፃል፡፡

ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት፣ አገራችንን ከተመፅዋችነት የሚያላቅቅ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጥና የዳበረ የገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት ከመገንባት እና ተጨማሪ እሴት ከመፍጠር አንፃር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ተቋም መሆኑን፣

ስድስቱ (6) የጨረሮች ቁጥር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እሴቶችና እምነቶችን ማለትም ደንበኛ ተኮር ምርጥ አገልግሎት መስጠት የሕብረተሰቡን ደህንነት መጠበቅ፣ ከብልሹ ምግባር የፀዳ የሥራ ከባቢ መፍጠር፣ ሙያና ክህሎትን ለተጨባጭ ውጤት መጠቀም፣ ሕግን ማስከበርና በቡድን መሥራትን ያመለክታሉ፡፡

ቤት

    የቤት ምልክቱ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ይገልፃል፡፡

የአገራችን ራዕይ እውን ከማድረግ እና የኢኮኖሚ ልማት አላማዎችን ከማሳካት አንፃር በዋናነት በራሷ ገቢ የምትተዳደር አገር መገንባትን፣ እና

ባለሥልጣበአዲስ አስተሳሰብ እየተገነባ ያለ ተቋም መሆኑን ይገልጻል፡፡

   
   
   
   
   

 

Visitors: Yesterday 107 | This week 732 | This month 1882 | Total 433261

We have 489 guests and no members online