የግብር መርሆች

Posted in Know How

አንድ የግብር ስርአት ሊከተላቸው ከሚገባ ዋናዋና መርሆች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ፍትሃዊነትን(እኩልነትንናገለልተኝነት) መጠበቅ:- የአገሪቱ የታክስ ስርዓት ሰዎች በሚያገኙት ገቢ ወይም በያዙት ሀብት አቅም በጎንዮሽና በሽቅቦሽ እኩል ግብር መክፈል እንዳለባቸው የሚያመለክት ነው፡፡ይህም ማለት ሰዎች ከሚያገኙት ገቢ ተመጣጣኝ የሆነ ግብር ልዩነት ሳይፈጥር ያለአድሎአዊነት እንደየዘርፉ መክፈል እንዳለባቸው የሚያመለክትነው፡፡

የታክስ ስርአቱ አስተዳደራዊ ወጪ ቆጣቢ መሆን፡- የታክስ ማስከፈያ ምጣኔው እና የታክስ ማዕቀፎቹ ይዘት ለመገንዘብና ለማስተዳደር ግለጽና ቀላል እንዲሆኑ በማድረግ የታክስ አከፋፈሉና ግዜው አመቺና በከፋዩ ላይ ውጣ ውረድ የማያስከትል እንዲሆን በማስቻል የታክስ አወሳሰኑና አሰባሰቡ የሚያስከትለው አስተዳደራዊ ወጪ ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግነው፡፡

ምርታማነት/ውጤታማነት፡- የታከስ ስርዐቱ የመንግስትን የወጪ ፍላጎት ለመሸፈን በቂ ገቢ ማስገኘት እንደሚገባውና በሂደት ከራስ በሚሰበሰበው ገቢየመንግሰትን አገልግሎቶችና መሰረተ ልማቶች ለማቅረብ የሚያስችለው መሆኑነው፡፡
እርግጠኛና ምቹ መሆን፡- የአገሪቱ የታክስ ስርአት የግብር ከፋዩ አጠቃላይ ገቢ፣ግብር የሚከፈለበት ገቢ እንዲሁም ከግብርከፋዩ የሚፈለግ የግብርና የታክስመጠን ላይ ለመድረስ የሚሰላበት አሰራር ወጥና በሁሉም ዘንድ በትክክል የሚታወቅ እንዲሆን ማድረግን የሚያመለክትነው፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው የግብር መርሆች ከሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው ወቅቱ የብር መክፈያ ጊዜ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በግብር መርህ መሰረት ለግብር ከፋዮቹ ፍትሀዊ፤ምቹና የተቀላጠፈ አገልግሎትን ለመስጠትዝግጅቱን አጠናቋል በተለይ የደረጃ *ሐ* ግብር ከፋዮች ግብራችሁን አሳውቃችሁ የምትከፍሉበት ጊዜ ከሐምሌ 1-ሐምሌ 30/2010ዓ.ም በመሆኑ ከወድሁ ግብራችሁን ኣሳውቃችሁ በመክፈል በመጨረሻው ቀን ከሚፈጠሩ ካላስፈላጊ እንግልት እራሳችሁን  በመጠበቅ ለአገልግሎት አሰጣጡ መሳለጥ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 428 guests and no members online