ግብር እዳ አይደለም

Posted in Know How

ግብር ለመንግሥት ዋናው የገቢ ምንጭ ሲሆን ለአንድ አገር ዕድገትና ብልጽግና የላቀ አስተዋፅኦ  ያበረክታል፡፡ግብር በአግባቡ መከፈሉ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ አገራት ጥቅሙ የላቀ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ አመታት ጦርነት፣ረሀብ፣በሽታናሞት መታወቂያዋ ነበሩ።የቃላት መፍቻ ምረሀብ(famine) የሚለውን ቃል ለማስረዳት ኢትዮጵያን እንደ ምሳሌነት አስቀምጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡አገሪቱ ቀድሞ በልመና የምትታወቅበት ገጽታም ነበር፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የምትታወቅበት የርሀብና የኃላቀርነት ተምሳሌት እየተለወጠ ይገኛል፡፡የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታን ስንቃኝ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ እናስተውላለን፡፡ዜጎችም የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነታቸው ከፍ እያለ ይገኛል፡፡ይህ ሁሉ የሆነው ታዲያ ዜጉች ከሚመነጨው ኢኮኖሚ የሚጠበቅባቸውን ግብር በመክፈላቸው መንግሥትም የሰበሰበውን የህዝብ ሀብት ለተገቢው አላማ በማዋሉ ነው፡፡

መንግሥት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጥ፣ህዝቡን ከኢኮኖሚ እድገቱ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ፣አገራችንን ከተመጽዋጭነት ማላቀቅና ዓለምአቀፍ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በቀጣይነት ማሻሻል መሰረታዊ ዓላማዎቹ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡በሂደቱም የተገኙ በርካታ ውጤቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡በታላቅ ህዝባዊ ስሜት እየተገነባ የሚገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታም አንዱ ማሳያ ነው፡፡ግንባታውን ዕውን ለማድረግ 80 ቢሊዮን ብር ገደማ ወጪ ይጠይቃል፡፡ግንባታው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ሙሉ ወጪ እየተከናወም ይገኛል፡፡ስራውተጠናቅቆአገልግሎትመስጠትሲጀምርከውስጥየኃይልአቅርቦትተርፎለጎረቤትአገሮችበሽያጭእንደሚቀርብናየገቢምንጭእንደሚፈጥርምይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ገቢው ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት እያደረገች ያለውን ዘርፈብዙ ጥረትያሳድጋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ-ጅቡቲና የአዲስአበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት የሀገሪቱን የልማት ማዕከላት በማስተሳሰርና ከጎረቤት ሀገር ወደቦችጋር በማገናኘት የጎላ ድረሻ እያጎለበተ ይገኛል፡፡እንዲሁም በርካታ የትምህርት ተቋማት፣ የጤና ተቋማት እና የመንገድ መሰረተ ልማትፕሮጀክትእየተተገበሩይገኛሉ፡፡

ታዲያ እነዚህና ሌሎች በስፋት እየተከናወኑ ያሉትን የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ዜጎች የሚከፍሉት ግብር ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡

በተጨማሪም  አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እየተገበረች ትገኛለች፡፡ለዕቅዱ ስኬማነት ከግብር ከፋዩ የሚሰበሰበው  ግብር የጎላጠቀሜታ እንደሚኖረው አያጠያይቅም፡፡በመሆኑም ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በወቅቱ ግብሩን አሳውቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ግብርን በወቅቱ አስታውቆ መክፈል ለዜጎች የተጣለ ግዴታ መሆኑንም እያንዳንዱ ዜጋ  መረዳትአለበት፡፡መንግሥት መሰረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማስፋፋት ኃላፊነት የተጣለበትን ያህል ዜጎች ደግሞ ግብር የመክፈል ግዴታእንዳለባቸው ሊያውቁ ይገባል፡፡

በመሆኑም መጭዎቹ ወራት አመታዊ ግብርን አስታውቆ መክፍያ ጊዚያት ስስለሆኑ ማንኛውም ግብር ከፋይ የሚጠበቅበትን ግብር  በታማኝነት አስታውቆ ሊከፍል ይገባል፡፡  ግብር ለስልጣኔ የሚከፈል ዋጋ እንጂ ዕዳ አይደለም፡፡ዕዳ የሚሆነው ግብር ከፋዩ የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ አሳውቆ ያልከፈለ እንደሆነ ነው፡፡በመሆኑም ለግብር ይታመኑ! ግብርዎን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ!የሚወዷት ሀገርዎንም ያልሙ!

በሰለሞን ዘሪሁን

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 601 guests and no members online