የኢንቨስትጌሸን ኦዲት ምንነት

Posted in Know How

ኢንቨስቲጌሽን ኦዲት ልዩ ሙያዊ የምርመራ ስልትን በመጠቀም በታክስ ማጭበርበር ወንጀል በሚጠረጠሩት ታክስ ከፋዮች ላይ ተገቢውን ምርመራ በማድረግና ወንጀልን ለይቶ በማውጣት ህግ ፊት እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድ በማስረጃ የተደገፈ ውጤት የሚቀርብበት የምርመራ ስራ ሲሆን ይህ ምርመራ መካሄድ ያለበት ህብረተሰቡ በግብር/ታክስ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ በሚያሳድግ መልኩ ነው፡፡

በልዩ ምርመራ ኦዲት ወቅት ኦዲተሮች ውሳኔ መስጠት ያለባቸው ከኢንቨስትጌሸን ኦዲት አላማ አንፃር ሲሆን የልዩ ምርመራ ኦዲት ዋና አለማ ተጠርጣሪ ግለሰብ ወንጀል መፈፀም አለመፈፀሙን በማስረጃ ማረጋገጥ ነው፡፡

ይህ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃዎችን (Fact and Evidence) በጥንቃቄ በማፈላለግ ሊፈፀም የሚገባ ተግባር ሲሆን የልዩ ምርመራ ኦዲት ዋና ተግባር ተብሎ ሊጠቀሱ የሚችሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

የቀረበውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ መረጃውን በጥልቀት መገምገምና መተንተን፣
የወንጀሉን መገለጫዎች መለየት፣
የወንጀሉን ተዋናዮች መለየት፣
የኦዲት ግኝቶችን በሚገባ አደራጅቶ ለዐቃቤ ህግ ለውሳኔ በሚረዳ መልኩ ማቅረብና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን ማከናወን፡፡

#በወንድዬብርሀኑ

Visitors: Yesterday 55 | This week 845 | This month 2340 | Total 454549

We have 939 guests and no members online