የወሮታ ክፍያዎች

Posted in Know How

 

የህገወጥ ዕቃዎች እንቅስቃሴ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ውስብስብ በመሆኑ ውጤታማ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ለመሥራት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከኮንትሮባንድ፣ ከንግድ ማጭበርበርና ህገወጥ ዕቃዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በይዘትም ሆነ በመጠን እየተበራከቱና እየተወሳሰቡ በመሄዳቸው በህጋዊ የንግድ እንቅስቃሴ፣ በመንግሥት ገቢ እንዲሁም በሕብረተሰቡ ደኅንነት ላይ አደጋ እያስከተሉ መጥተዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ህገወጥ ድርጊት በተጠናከረ መልኩ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስልቶችን መዘርጋት አስፈልጓል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ሌሎች የጉምሩክ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ መረጃ ወሳኝ በመሆኑና ለዚህም አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ጠቋሚዎች፣ ያዦች፣ ተባባሪዎችና ደጋፊዎች ካደረጉት ተሳትፎ ጋር የተመጣጠነ ወሮታ ሊከፈላቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ የጉምሩክ ክልል በየትኛውም ስፍራ ህገ-ወጥ ዕቃ መኖሩን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ወዲያውኑ በአቅራቢያው ለሚገኝ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወይም ህግ አስከባሪ አካል ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ በሚደርግበት ጊዜ ጥቆማ ከማይቀርብባቸው ሁኔታዎች በስተቀር ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚቀርብ ጥቆማ ወይም ያለምንም ጥቆማ ህገወጥ ዕቃ ከተያዘ እና ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ከተደረገ የህገወጥ ዕቃዎች መረጃ አሰጣጥ፣ አያያዝ፣ አመዘጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን መመሪያ ቁጥር 78/2004 መሠረት የወሮታ ክፍያ እንደሚከተለው ይከፈላል:-

1.  በቀረጥነጻ የገባን ዕቃ በማስተላለፍ ለጠቋሚ፣ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 20 በመቶ፣

ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ እና

ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 30 በመቶ የወሮታ ክፍያ         ይከፈላል፡፡

2.  በኮንትሮባንድ የሚገባ ዕቃን ለጠቆመ፣ ለያዘ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረገ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 40 በመቶ፣

ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ እና

ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 50 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

3.    በኮንትሮባንድየሚወጣ ዕቃን ለጠቆመ፣ ለያዘ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረገ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 40 በመቶ እና

ለ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 50 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

4.  የንግድ ማጭበርበርን ለጠቆመ፣ ለያዘ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረገ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 15 በመቶ እና

ለ/ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

5.  እሽጎችን በመፍታት የተፈጸመ ህገወጥ ተግባርን ላጋለጠ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 30 በመቶ፣

ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ እና

ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 40 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

6.  ሽያጭ ላይ የማይውሉ ህገወጥ ዕቃዎች ሲያዙ ስለሚከፈል የወሮታ ክፍያ መጠን፤

·         ህገወጥ ዕቃው ልባሽ ጨርቅ ከሆነ የወሮታ ክፍያ መጠኑ በኪሎ ብር 25 እንዲታሰብ ተደርጎ:-

   ሀ/ ለጠቋሚ 25 በመቶ፣

 ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 15 በመቶ እና     

                  

           ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 50 በመቶ        የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

·         ህገወጥ ዕቃው በሚመለከተው መስሪያ ቤት የሽያጭ የገበያ ዋጋ የወጣለት ከሆነ የዚህኑ ዋጋ:-

     ሀ/ ለጠቋሚ 20 በመቶ፣

           ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 15 በመቶ እና

           ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 40 በመቶ   የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

·         ህገወጥ ዕቃው የሽያጭ የገበያ ዋጋ ሊወጣለት የማይችል ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚሰይመው ከ3 ያላነሱ አባላት ያሉበት ቡድን አማካኝነት እንደየዕቃው ባህሪ እየተጣራ ቡድኑ ለዕቃው ከሚሰጠው ዋጋ ላይ:-                     

    ሀ/ ለጠቋሚ 10 በመቶ፣

           ለ/ ለያዥ፤ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 5 በመቶ እና

           ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 30 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

7.  ህገወጥ ገንዘብ ሲያዝ ስለሚከፈል የወሮታ መጠን፤

·         የተያዘው ህገወጥ ገንዘብ የውጭ ሀገር ገንዘብ ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ ብር ከተመነዘረ በኋላ ከዚሁ ብር፤

ሀ/ ለጠቋሚ 15 በመቶ፣

      ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ እና

       ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 30 በመቶ   

          የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

·         የተያዘው ህገወጥ ዕቃ የኢትዮጵያ ብር ከሆነ ከዚሁ ላይ፤

ሀ/ ለጠቋሚ 15 በመቶ፣

ለ/ ለያዥ፣ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ 10 በመቶ እና

ሐ/ ዕቃው የተያዘው በሕግ አስከባሪ አካል ሲሆን ለተቋሙ 35 በመቶ የወሮታ ክፍያ ይከፈላል፡፡

በጠቋሚ፣ በያዥ፣ ድጋፍና ትብብር በማድረግ ሂደት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች በጋራ ከጠቆሙ፣ ከያዙ፣ ድጋፍና ትብብር ካደረጉ የወሮታ ክፍያው እንደየድረሻቸው ተካፍሎ ተፈጻሚ ይደረግላቸዋል፡፡

በሰሎሞንደግአረገ

 

Visitors: Yesterday 2 | This week 102 | This month 1486 | Total 459629

We have 710 guests and no members online