ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር (ሠንጠረዥ “ሀ”)

Posted in Know How

ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ወይም ድርጅት ነው ሲሆን ተቀጣሪማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡

  ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው ደመወዝ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣

ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣

ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ሰው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣

(ሠንጠረዥ “ሀ”) ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች

ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግበሩ ይሰላል፡፡

በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰንበት ሁኔታ በደንብ ይወሰናል፡፡

 

ተ.ቁ

የሚገኝ የወር ገቢ በብር

ተከፋይ የገቢ ግብር በመቶኛ

1

0 - 600

ነፃ

2

601 – 1650

10

3

1651 - 3200

15

4

3,201 - 5,250

20

5

5,251 - 7,800

25

6

7,801 - 10,900

30

7

10,900 - በላይ

35

 

ከመቀጠርየሚገኙገቢዎችከግብርነፃስለመሆን

የሚከተሉትከመቀጠርየሚገኙገቢዎችከግብርነፃይሆናሉ፡፡­

ሠራተኛውሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤

በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤

በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤

ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤

የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤

የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤

ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤

በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ  እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤

የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤

በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-

ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ፤

  ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፤

በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን ወይም በታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 135 መሠረት የሚሰጥ ሽልማት፤

በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤

በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤

በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤

ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤

ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤

ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤

በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤

ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤

በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡

የሚኒስትሮችምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ ይችላል፡፡

 

 

Visitors: Yesterday 6 | This week 1 | This month 2203 | Total 824986

We have 384 guests and no members online