የተገልጋዮች ቻርተር

Posted in Know How

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዘመናዊ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ሥርዓት በመዘርጋት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት፣ ኮንትሮባንድን፣ የታክስ ማጭበርበርንና ስወራን በመከላከልና በመቆጣጠር፣ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የታክስ ገቢ በብቃትና በወቅቱ ለመሰብሰብ በአዋጅ ቁጥር 587/2000 የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ሲፈጽም በታክስ እና ጉምሩክ ህጎች ለታክስ ከፋዮች የተሠጡ መብቶች ያከብራል፡፡ ታክስ ከፋዮችም በታክስ ህጎች መሠረት ታክስ መክፈል የዜግነት ክብር ነው በሚል መርህ ግዴታቸውን በፈቃደኝነት እንደሚወጡ ይተማመናል፡፡

ይህ የተገልጋዮች ቻርተር ከላይ በተገለጸው መሠረተ ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ የተገልጋዮችን መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ በማስቀመጥ ተገልጋዮች ከተቋሙ የሚያገኙዋቸውን አገልግሎቶችና የአገልግሎትአሰጣጥስታንዳርዶችንለማሳወቅናበዚህመሰረት  አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ለመግለጽ የተዘጋጀ ሠነድ ነው፡፡

ቻርተሩ በአሁን ወቅት ያለውን የተገልጋዮች ፍላጎት፣ የመሰል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ተቋማትን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን በጊዜ ሂደት የሚከሰቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኖሎጂያዊ ለውጦችን በማገናዘብ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማሟላት በሚያስችል ሁኔታ የሚከለስና የሚሻሻል ይሆናል፡፡

የተቋሙ ዓላማዎች ስልጣንና ተግባር፣ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ የባለሥልጣኑ ተገልጋዮች ፣ የሚሰጡ የአገልግሎት ዓይነቶች፣ አገልግሎቶቹ የሚሰጡባቸውን ቦታዎችና ስታንዳርድ፣ የተገልጋዮችን መብትና ግዴታዎች፣ አስተያየት ወይም ግብዓት የሚሰጥበት ሂደት፣ የቅሬታ አቀራረብ፣ክትትልና የግምገማ ሥርዓት፣ እንዲሁም መረጃ የሚሰጥበትን መንገዶች እና ተጠያቂነት በቻርተሩ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው፡፡

Document titel:-የተገልጋዮች ቻርተር

Click to download

Add comment

We want to hear from you and strive to make our Website better and user friendly.

Please don't ask Questions here bcz there is a forum link for questions and answers since you may not get an answer from Feedback.


Security code
Refresh

Visitors: Yesterday 6 | This week 1 | This month 2203 | Total 824986

We have 388 guests and no members online