የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ማለት ምን ማለት ነው?

Posted in Know How

የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ማለት የአንድ አስመጪ ወይም ላኪ ዕቃ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈጽሞበት ከተለቀቀ በኋላ የዕቃውን ዲክለራሲዮን፤ የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓትና የተያዙ መረጃዎች ትክክለኛነት ለማጣራት እና የድርጅቱን የሕግ ተገዥነት ሁኔታ ለማረጋገጥ ከንግድ ሂደቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው መዛግብት፣ የንግድ አሠራሮችን እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉምሩክ ነክ የንግድ መረጃዎችን የመመርመር ተግባር ሲሆን የዓለም አቀፍ ተሞክሮ በተሸሻለው ኪዮቶ ኮንቬንሽን ስምምነት መሠረት የተፋጠነ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ዕቃ ከተለቀቀ በኋላ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የተፈጠረና በአለም አቀፍ የጉምሩክ ድርጅት /WCO/ ስምምነት መሠረት በአባል አገራት አየተሰራበት ያለ አሠራር ነው፡፡

የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲትለምን አስፈለገ? ጠቀሜታውስ?

የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲት በዋናነት ፡-

1. የንግድ ስርዓቱን ለማሳለጥ/ ለማቀላጠፍ/ ያስችላል

የስጋት ስራ አመራር እና ቀላል የጉምሩክ የዕቃ-አወጣጥ  ስርዓት በመጠቀም  በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ የሚስተናገዱ ዕቃዎች ላይ አካላዊ ፍተሻ ሳይከናወን በተፋጠነ መልኩ በአጭር ጊዜ ለመልቀቅ ያስችላል፤ (ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ያለባቸውን ሰነዶችና ዕቃዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያላቸውን ሰነዶች በድህረ-ዕቃ አወጣጥ እንዲታዩ ማድረግ ያስችላል)፡፡

2. በጉምሩክና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ትብብርና በጋራ የመስራት ባህልን ያዳብራል

የስጋት ስራ አመራር ስርዓትና የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲትን በመጠቀም ጉምሩክ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት መልካምና የተሻለ ከማድረጉ በተጨማሪ ለአንድ ዓላማ የመስራት ባህልን ያዳብራል፡፡

3. የህግ ተገዥነትን ያጎለብታል

በደንበኞች ላይ እምነትን በማሳደር ዕቃዎቻቸው በቀላል የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት እንዲለቀቁ በማድረግ በተወሰነ ወቅት ዕቃዎች ወደ አገር ሲገቡ ወይም ከአገር ሲወጡ ለጉምሩክ ቀርበው የነበሩ ሰነዶች በመመርመር የአስመጪዎች/ላኪዎችን የህግ ተገዥነት ደረጃ ለማጎልበት ያስችላል

4. የተቋሙን የሰው ሃይል በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል

የስጋት ሥራ አመራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ተቋሙ ያለውን ውስን የሰው ሃይል የንግድ እንቅስቃሴው ሳይጎዳ ተፈላጊው ውጤት በሚያስገኝና በተገቢ ቦታ በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል፡፡

5. ከጉምሩክ የሚሰበሰበውን ገቢ ይጨምራል

ተገቢው ክህሎት፣ ዕውቀትና የሙያ ብቃት ያለውን ሰራተኛ በመመደብ በወቅቱ ሳይሰበሰብ ቀርቶ የነበረን የመንግስት ቀሪ ቀረጥና ታክስ በህግ በተቀመጠው አግባብ እንዲሰበሰብና የተቋሙ ገቢ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡

6. ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ከጉምሩክ የሚለቀቁበትን ጊዜ/ሰዓት ይቀንሳል

በስጋት ሥራ አመራር መስፈርት መሠረት የተለዩና በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ የተስተናገዱ ዕቃዎችን /ሰነዶችን/ በቀላል የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በአጭር ጊዜ መልቀቅ ያስችላል፡፡

7. ወጪን ይቀንሳል

ውጤታማ የስጋት ሥራ አመራር ስርዓት በመዘርጋትና ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያላቸውን የገቢና ወጪ ዕቃዎች የጉምሩክ ጣቢያ በደረሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመልቀቅ ተቋሙ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ለስራው የሚያውሉትን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ መቀንስ ያስችላል፡፡

8. ንግዱ ማህበረሰብ / ደንበኞች/ዕውቀት አንዲጨምር ይረዳል

የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲትን በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል ኦዲት ተደራጊ የንግዱ ማህበረሰብ በራሳቸው ተነሳሽነት የሚጠበቅባቸውን ቀረጥና ታክስ በወቅቱ እንዲከፍሉና የህግ ተገዥነታቸው እንዲዳብር ያደርጋል፡፡

የድህረ-ዕቃ አወጣጥ የመስክ ኦዲት ለማከናዎን መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡

  • የጉምሩክ ዲክለራሲዮን፣

  • የዲክለራሲዮን ፍሬ ነገር መግለጫ (declaration of facts /VDD)

  • የስሪት ሀገር ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ( Certificate of Origin  )

  • የዋጋ ሰነድ (invoice)

  • የዕቃ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ (packing list)

መዛግብት

1. ከድርጅቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው መዛግብት (business related document)

የመረጃ ልወውጥ የተደረገባቸው የፅሁፍ ወይም ኤልክትሮኒክ ሰነዶች (Correspondence፡  like letters, telegrams, telefaxes, E-mails etc.. .

የስራ ወይም የንግድ ስምምነት   የተደረገባቸው ልዩ ልዩ ሰነዶች ወይም ውሎች (Contract agreements)

የጭነትና የዕቃ የማጓጓዣ  ሰነዶች

የግዥና ሽያጭ ሰነዶች /ደረሰኞች

2. ከሂሳብ መዛግብት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰነዶች

የግዥጥያቄ የቀረበባቸው/ Purchase orders/፣ የግዥ ደረሰኞች / Invoice/፣ የማስጫኛ መረጃዎች/Shipping document/፣

የባንክየግንኙነት ሰነዶች Debit/Credit notes፣ የባንክ ሂሳብ መግለጫ/ Bank statement and Bank Permits) የገንዘብ መቀበያ ደረሰኞች/ Receipts/, ክፍያ የተፈፀመባቸው የባንክ ቼኮች/Checks/ እና ሌሎች ሰነዶች ወይም መረጃዎች፡፡

3. የሂሳብ መዛግብት : ከድርጅቱ የስራ እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታ የሚገናኙና በድርጅቱ መያዝ የሚገባቸው

የሂሳብመዝገብ/Book of Account/፣ አጠቃላይ መዝገብ/ General journal/፣ ዝርዝር የሂሳብ ቋት/General ledger/፣ ደጋፊ መዝገቦች/ Subsidiary journal ለምሳሌ ፡- የሽያጭ / Sales/፣ የግዥ / Purchas/ መዝገቦች፣ የገንዘብ መቀበያና መክፈያ ቮቸር/Cash receipt & Cash payment vouchers እና ሌሎች ሰነዶች፤

ደጋፊ የሂሳብ ቋቶች/ Subsidiary ledger/ ለምሳሌ፡- የተስብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች ቋት/ Account receivable & Account Payable/፣ የንብረት  ቆጠራ ሪፖርቶች/Merchandise Inventory/፣ የቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች መረጃዎች/ Plant and Equipment  እና ሌሎች ተዛማጅ ማስረጃዎች

4. የሂሳብ መግለጫ ሰነዶች፡ Cash flows statement፣  balance sheet statement, Income statement ,Trial balances, Worksheet, Bank reconciliation etc.

 

Visitors: Yesterday 118 | This week 255 | This month 1971 | Total 822265

We have 226 guests and no members online