የኢ/ገ/ጉ/ባ ከኢትዮጵያ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እና ሶፍትዌር አቅራቢዎች ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ፤

Posted in Latest News

የባለስልጣን  መ/ቤቱ  ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ በተገኙበት ጥቅምት 30/2010ዓ.ም በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት  ለሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የመለዋወጫ አቅርቦት፣የመሣሪያዎች ጥገና እና በአሠራር ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ለመፍታት ማህበሩ ከባልስልጣን መ/ቤቱ ጋር ተቀራርቦ የሚሰራበትን ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም የማህበሩና የተቋሙ አመራሮች በየሦስት ወሩ ቋሚ የግንኙነት ጊዜ እንዲኖራቸው በመስማማት ከተጓዳኝ መ/ቤቶች አመራሮች ጋርም የጋራ መድረክ በማካሄድ የሚስተዋሉ የአሠራር ችግሮች የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ባለስልጣን መ/ቤቱ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

 

Visitors: Yesterday 115 | This week 333 | This month 2159 | Total 405078

We have 230 guests and no members online