የ2009 የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም እና የ2010 የመልካም አስተዳደር እቅድ ላይ ከግብር ከፋዮችና ከህዝብ ክንፍ ጋር ውይይት ተካሄደ፤

Posted in Latest News

ለውይይቱ መነሻ በ2009 ዓ.ም. የተስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የ2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ በአቶ ያሬድ ፍቃዴ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ለተሳታፊዎቹ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም የቀረቡትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቋሙ የለየበትን አግባብ አድነቀዋል፡፡

አቶ ያሬድ ፈቃደ ቀልጣፋና፣ ፍትሃዊና ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት ለግበር ከፋዮች መስጠት ባልተሟላበት ሁኔታ ንግድና ኢንቨስትመንት ሊበረታታ ስለማይችል የመልካም አስተዳደር ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት መዝገብ ተሳታፊዎች ከቀን ገቢ ግምቱ ጋ በተያያዘ፣ ከሂሳብ መዝገብ አያያዝና ከደረሰኝ አቆራረጥ ጋር ተያይዞ ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች በተሳታፊዎቹ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ በመድረኩ በመገኘት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም በ2010 የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታት አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሂዶ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Visitors: Yesterday 1 | This week 163 | This month 1229 | Total 407134

We have 287 guests and no members online