ባለስልጣኑ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይሆን አደረኩኝ አለ፤

Posted in Latest News

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የ2009 በጀት አመት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀምና የ2010 ዓ.ም. የመልካም አስተዳደር እቅድ በተመለከተ ህዳር 14/2010 ዓ.ም. ከህዝብ ክንፍና ከነጋዴው ማህበረሰብ ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይት አካሂዷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤቶች ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ፈቃዴ እንደተናገሩት የሽያች መመዝገቢያ መሳሪያ የመልካ አስተዳደር ችግር እንደሆነ አድርገናል ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት ግብር ከፋዩ ወደቅጣት እንዳይገባ በአሰራርና በተቴክኖሎጂ ለማገዝ በሂሳብ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ሶፍዌረወ እንዲገጠምባቸውና የአመታዊ የማደሻ ጊዚያቸውን ከአራት ጊዜ በላይ ደጋግሞ ለግብር ከፋች በሂሳብ መመዝገቢያ መሳሪያ አማካኝነት መረጃ እንዲሰጥ/እንዲያስታውስ የሚያስችል አሰራርን ተግባራዊ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ከቀን ገቢ ግምቱ ጋር በተያያዘ ከደረጃ ሐ ወደ ደረጃ ለ ያደጉ ግብር ከፋዮች የሽያች መመዝገቢያ መሳሪያ ገዝተው የሚጠቀሙበትን የአድ አመት የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው መደረጉ ተገልጿል፡፡

Visitors: Yesterday 1 | This week 162 | This month 1228 | Total 407133

We have 269 guests and no members online