የአዲስ አበባ ታክስ ፕሮግራም ልማት ስራዎች ዘርፍ የ2009 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡

Posted in Latest News

በ2009 በጀት ዓመት እቅድ ከተቀመጠለት ግብ አኳያ በምን ያህል ደረጃ እንደተሳካ ለመገምገም አመራሩም ሆነ ፈፃሚው የመማማር እድል እንዲኖራቸው በማድረግ ለቀጣይ ግቦች አቅም የመፍጠር ዓላማ ያነገበ ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ህዳር 18/2010 ዓ.ም በቢሾፍቱ ተጀምሯል፡፡

የ2010 የውይይቱን ሂደት በተመለከተ እቅዳችንን ከግብ ለማድረግ በግልፀኝነት ላይ የተመሰረተና በውስጥ ችግሮች ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ አለበት ሲሉ የኢ/ገ/ጉ/ባ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ ገልጸዋል፡፡ 

መድረኩን የከፈቱት የሞደርናይዜሽንና ኮርፖሬት ስራዎች ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ንጉሴ በአ/አ ዘርፍ በ2009 በጀት ዓመት የነበረውን የ11 በመቶ ወይም የ3 ቢሊዮን ብር የእቅድ አፈፃፀም ክፍተት በ2010 በጀት ዓመት እንዳይደገም የነበሩ ችግሮችን በጥልቀት ዳሰን እና ለይተን በማውጣት መፍትሔ ማስቀመጥ አለብን ብለዋል፡፡

በውይይቱም የ2009 በጀት ዓመት የልማታዊ የታክስ ስርዓት ግንባታ አፈፃፀም፣ የዘመናዊ የታክስ ስርዓት ግንባታ ስራ ያለበት ደረጃ፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት፣ የህግ ተገዥነት የማስፈን ስራ እና የታክስ ኦዲት ስራዎች በጥልቀት የሚዳሰሱ አጀንዳዎች ናቸው፡፡

የውይይት ጊዜው ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚዘልቅ ሲሆን፣ በመደምደሚያው የ2010 በጀት ዓመት የአራት ወራት አፈፃፀም በመገምገም እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለተግባራዊነቱ ስምምነት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ የሁሉም የአ/አበባ ቅ/ጽ/ቤቶች ስራ አስኪያጆች ም/ስራ አስኪያጆች እና በዘርፉ ያሉ ቡድን አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

Visitors: Yesterday 1 | This week 163 | This month 1229 | Total 407134

We have 284 guests and no members online