በጅማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የ2010 የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተጠናቀቀ

Posted in Latest News

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በጅማ ከተማ በሚገኙ 40 የ1ኛ፣ የ2ኛ እና የመሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች መካከል በግብር ወይም ታክስ እና ኮንትሮባንድ ጉዳዮች ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ጥያቄና መልስ ውድድር ሰኔ 23/2010 ዓ.ም. ተጠናቀቀ፡፡

በማጠቃለያ ውድድሩ የጅማ ከተማ እና የዞን ባለድርሻ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የገቢ ዘርፍ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ አርአያ ግብር ከፋዮች፣ ከ40 ት/ቤቶች የተውጣጡ የግብር እና ታክስ ክበብ አስተባባሪ መምህራን፣ ከ2ኛ ዙር ጀምሮ በውድድሩ ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ተማሪዎች፣ የተወዳዳሪ ተማሪዎች ቤተሰብ እና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በጅማ ከተማ በሚገኙ የ1ኛ፣ የ2ኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች መካከል በሶስት ዙር በተካሄደው በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ 12 ተማሪዎች፣ ስምንት አስተባባሪ መምህራን እንደየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማትና ለስድስት ት/ቤቶች የግብር እና ታክስ ክበብን ለማጠናከር የሚያግዙ ግብአቶች ማለትም ሁለት ሞንታርቦዎች እና አራት ጂፓሶች ሽልማት በመስጠት ውድድሩ እንደተቋጨ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

Visitors: Yesterday 146 | This week 520 | This month 1516 | Total 435889

We have 426 guests and no members online