በኤች አይ ቪ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

Posted in Latest News

በገቢዎች ሚኒስትር የኤች አይ ቪ ቀንን አስመልክቶ ከዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተሰበሰበ ገንዘብ ወላጆቻቸውን ላጡና ለተቸገሩ አስር ህጻናት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ችግርተኛ ህጻናትን መርዳት እንደሚገባ በሚኒስቴሩ የተቋማዊ አቅም ግንባታና ድጋፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ምህረት ምናሰብ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰራተኞችና ሌሎች በበሽታው የተጎዱ ህጻናት ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡

በአጠቃላይ በተቋሙ 160 ተረጂዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከተቋሙ ውጪ ያሉ አስራ ሶስት አረጋውያንን እንዲሁም ለ79 ችግርተኛና ለኤች አይ ቪ ተጎጂ ለሆኑ የተቋሙ ሰራተኞችና የሰራተኛ ቤተሰቦች ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በየወሩ ከተቋሙ ውጪ ላሉ ተረጂዎች የአምስት መቶ፣ ከተቋሙ ሰራተኛና ቤተሰቦች የአንድ ሺ ብር ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከቦሌ ክ/ከተማ የተወጣጡ አስር ህጻናትን ለመርዳት በዛሬው እለት ተረክቦ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታዋ ተረባርበን በመስራት ከጥቃት ነጻ ሆና አስተማማኝ ገቢ ያላት ሀገር ለመፍጠር ተባብረን እንስራ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 489 guests and no members online