“የሂሳብ መዝገብ ብንይዝም በግምት ይተመንብናል ”ግብር ከፋዮች

Posted in Latest News

ገቢ እና ወጭያችንን የሚያሳይ የሂሳብ መዝገብ ብንይዝም ግብር በግምት ይወሰንብናል ሲሉ ግብር ከፋዮች ቅሬታቸውን አቀረቡ ፡፡
በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979 /2008 በተደነገገው መሰረት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸው የሚሰላው መዝገባቸውን መሰረት አድርጎ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡

ይሁን እንጂ የገቢዎች ሚኒስቴር ከምስራቅ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ጋር ባደረገው ውይይት ዓመታዊ ገቢ እና ወጭያችንን የሚያሳ የሂሳብ መዝገብ ብናቀርብም መዝገባችን ውድቅ ሆኖ ግብር በግምት ይተመንብናል ብለዋል፡፡

በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ወቅት ወጭን ማጋነን ፣ገቢን ማሳነስ ሀሰተኛ ደረሰኝ መጠቀም ፣ በአጠቃላይ ህገ ወጥ የንግድ አካሄድ ተከትሎ የተዘጋጀ የሂሳብ መዝገብ ውድቅ እንደሚደረግ የቅ/ጽ/ቤቱ የህግ ማሰከበር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጂ አቶ አልማው አላምረው ተናግረው በተጨማሪም ገለልተኛ ጥቆማዎችን በመቀበል ከንግድ ቦታው አካላዊ ምልከታ በማድረግ ግምት እንደሚገመት ተናግረዋል፡፡

አቶ አልማው አያይዘው ሂሳብ መዝገብ የተቋሙ እና የግብር ከፋዩ መተማመኛ ሰነድ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ትክክለኛ ሂሳብ መዝገብ በመያዝ ከግምት ነጻ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡
#በየሺወርቅ ተጫነ

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 597 guests and no members online