በጠረፍ አካባቢ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ለታለመለት ዓላማ እየዋለ እንዳልሆነ ተገለጸ

Posted in Latest News

ከመሀል ሀገር ለሚርቁና የመሰረተ ልማት ላልደረሰባቸው የጠረፍ አካባቢ ማህበረሰብ የእለት ፍጆታና እቃዎች እንዲሁም አልባሳት በቀላሉ እንዲያገኙ ታስቦ የተፈቀደው ፍራንኮቫሉታ ከታሰበለት አላማ ውጭ በመዋል የኮንትሮባንድነት ባህሪይ እየያዘ መምጣቱን የገቢዎች ሚኒሰቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አበቤ ተናገሩ፡፡

በዚህም ምክኒያት ከጠረፋማው አካባቢ ይልቅ መዳረሻውን መሀል አገር የማድረግ ዝንባሌ እየታየ በመምጣቱ በነጋዴው ላይ የፍትሀዊነት ችግር ከመፍጠር ጀምሮ ለሀገር ውስጥ ምርትና ለኢንቨስትመንት እንቅፋት በመሆን የጥቂት ግለሰቦች ሀብት ማፍሪያ እየሆነ መጥቷል ሲሉ ሚንሰተሯ ገልጸዋል፡፡

ይሄው የፍራንኮ ቫሉታ ጉዳይ መንግስትንም በሶስት አመት ውስጥ ብቻ ለልማት ሊውል ይችል የነበረን 14.3 ቢሊዮን ብር አሳጥቶታል ተብሏል፡፡

በመሆኑም መንግስት የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ መከላከል የሚያስችል የውሳኔ ሀሳብ እንዳስተላለፈ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ ለተወያዮች ገልጸዋል፡፡
#በጌታቸውተሾመ

Visitors: Yesterday 55 | This week 845 | This month 2340 | Total 454549

We have 870 guests and no members online