ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት የሚደረግ ቅንጅታዊ አሰራር ተጠያቂነትን ሊፍጠር በሚችል መልኩ መሆን እንዳለበት ተገለጸ

Posted in Latest News


ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከልና ችግሩን መፍታት እንዲቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደረግ ቅንጅታዊ አሰራር እቅድን መሰረት ያደረገ እና ተጠያቂነትን መፍጠር በሚችል መልኩ መሆን እንዳለበት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አበቤ ህዳር 23/ 2011ዓ.ም. በሃዋሳ ከተማ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር በኮትሮባንድና ህገወጥ ንግድ መከላከል ዙሪያ በተካሄደ የንቅናቄ መድረክ ላይ ገለጹ፡፡

ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠኑ እና በዓይነቱ እየጨመረ በመምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ወ/ሮ አዳነች ጠቁመው በዚህም በአገር ደህንነት እና ጸጥታ ብሎም አኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል የማይባል ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በገቢ ዘርፉም የገቢ አሰባሰቡን በመቀነስ በአገሪቱ ልማት እንቅስቃሴ ላይ የማዳከም ሁኔታ እየተፈጠረ የሚገኝ መሆኑን ይህን ጸረ ልማታዊ ተግባር መቀልበስ የሚያስችል አደረጃጀት፣ አሰራር እና ቅንጅት ተግባራዊ በማድረግ በእቅድ ላይ የተመራ ተጠያቂነትን ሊፈጥር እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በመቀነስ፤ የሃገር ሃብት የምንላቸው እንደ ማእድን፣ የቀንድ ከብት፣ የግብርና ምርቶች እና የመሳሰሉት በህገወጥ መንገድ ከሃገር በህገወጥ መንገድ እየወጡ መሆናቸውና ይህም አገሪቷ ከዚህ ቀላል የማይባል ገቢ እያጣች እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

በውይይቱም ላይ የተገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ሃላፊዎች የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት የአጭር፣ የመካከለኛ እና ረዥም ጊዜ እቅድ በማውጣት እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡
#በዳዊትአለሙፈይሳ

Visitors: Yesterday 55 | This week 845 | This month 2340 | Total 454549

We have 943 guests and no members online