ዓመታዊ ገቢያቸው ከ3 ሚሊዮን እስከ 100ሚልዮን ብር የሆኑ ግብር ከፋይ ድርጅቶችን ሊያስተናግድ የሚችል መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት መከፈቱ ተገለፀ፡፡****

Posted in Latest News

ታህሳስ 03/ 2011ዓ.ም የገቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ቅ/ፅ/ቤቱን ለግብር ከፋዮች አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር መርቀው ከፍተዋል፡፡

ቅ/ጽ/ቤቱ የተከፈተው ለግብር ከፋዮች የአገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ለማድረግ እና ግብሩን በብቃት መሰብሰብ እንዲያስችል ነው ሲሉ ሚንስትሯ ገልጸዋል፡፡

ሰራተኞቹም ደንበኞቻቸዉን በደስታ እንደሚያስተናግዷቸው እምነቴ ነው ሲሉ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳስበዋል፡፡

ከምዕራብ፣ ከምስራቅ እና ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የተዉጣጡ 4,482 ግብር ከፋዮች መሆናቸውን የቅ/ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ብርቱካን ግርማ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ግብር ከፋዮቻችን ብናሳዉቃቸው፣ ብናስተምራቸው፣ ብንደግፋቸው እና ፈጣን አገልግሎት ብንሰጣቸው ለገቢያችን መዳበር እና በጊዜው መሰብሰብ ይበልጥ አስተዋፅኦ ያደርጉልናል በማለት ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል፡፡
#በገነትተስፋዬ

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 470 guests and no members online