የሰራተኞች ድልድል የሰራተኞችን ብቃትና ውጤታማነት መሰረት ያደረገ እንደሆነ ተገለፀ

Posted in Latest News


የሰራተኞች ድልድል የሰራተኞችን ብቃትና ውጤታማነት መሰረት ያደረገ መሆኑን የሰራተኞች ድልድልና ምደባ ሂደት ይፋ በተደረገበት ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

በአገር ደረጃ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና በማደራጀት በሚኒስቴር ደረጃ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ተጠሪነቱ ለገቢዎች ሚኒስቴር የሆነ የጉምሩክ ኮሚሽን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

ለዚህም አገራዊ የለውጥ ሂደቱን ማስቀጠል የሚችል እና ለሚኒስተር መ/ቤቱ የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ ሊያሳካ የሚችል ብቃት ያለው ሰራተኛን ውጤት ማምጣት በሚችልበት የስራ መደብ ላይ መመደብ አስፈላጊ በመሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር የሰው ሃይል ድልድል አፈጻጸም መመሪያ 140/2011 አውጥቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በመመሪያው መሰረትም ሰራተኞች ባላቸው የስራ ልምድ፣ የስነ-ምግባር ሁኔታ እና የስራ ውጤታማነትን መሰረት በሚመጥናቸው ቦታ እንደተደለደሉ እና ድልድሉም የፆታ ተዋፆን እና ፍትሀዊ አሰራርን መሰረት የደረገ እንደሆነ ሚኒስትሯ አክለው ገልፀዋል፡፡

በአመራር ደረጃ ላይ ያሉ የሰራተኞች ድልድል ቀደም ብሎ የተከናወነ ሲሆን በፈጻሚ ደረጃ ያሉ የሰራተኞች ድልድል ደግሞ በዛሬው ዕለት በድልድል ኮሚቴው ይፋ ሆኗል፡፡ ሰራተኞችም ድልድሉን ካዩ በኋላ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም ሰራተኛ ውጤት ለማምጣት ተያይዞና ተቀናጅቶ ስራዎችን በጥራትና ለውጡን ሊያስቀጥል በሚችል አግባብ መስራት እንዳለበት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡

Visitors: Yesterday 55 | This week 845 | This month 2340 | Total 454549

We have 941 guests and no members online