የአመራሩን አቅም ለማጎልበት የስራ አመራር ስልጠና ተሰጠ

Posted in Latest News

ለገቢዎች ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች በትራንፎርሜሽናል አመራርና በአመለካከት ወይም አተያይ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ በታክስ ትራንስፎርሜሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር አዲስ ታምሬ በኔክሰስ ሆቴል ጥር 5/2011 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ እና ሀብት አስተዳደር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ምህረት ምንአሰብ የተሰጠው ስልጠና ግብር ከፋዮችንም ሆነ ሰራተኛውን በአግባቡ በመያዝ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ያቀዱትን እቅድ በማሳከት በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ተገዢነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ በበኩላቸው ስልጠናው ራሳቸውን ማየት ያስቻለቸው መሆኑን ተናግረው ከዚህ በኃላ ሁላችንም ‹‹አመራር ሁነን እንገኝም›› ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

የተለወጠ አስተሳሰብ ይዞ ለመቀጠል ከመሪዎች የሚጠበቅ ብዙ ነገር መኖሩን ያነሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ እያንዳንዱ አመራር ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ ለልቡ አዉጆ ሊነግረው ይገባል ብለዋል፡፡

መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንድሚቀጥሉና በቀጣይም በተመሳሳይ መንገድ ለፈጻሚውም ስልጠናው እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
#በጌታቸውተሾመ

Visitors: Yesterday 113 | This week 114 | This month 1290 | Total 448649

We have 459 guests and no members online