በየትኛውም ጊዜ ከህዝብ አይን የሚሰወር ነገር የለም

Posted in Latest News

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3 04183 ሱማ የጭነት መኪና 692 ከረጢት ሩዝ፣93 ካርቶን ሳሙናና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከውጭ ጭኖ ወደ ጅግጅጋ ለማስገባት ሲሞክር የካቲት 25/2011 ዓ.ም ለሊት 9 ሰዓት ቀብሪባያ በተባ ስፍራ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገልጸዋል፡፡

በፌደራል ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋሉም የተገለጸ ሲሆን የእቃዎቹ ግምታዊ ዋጋም 433 ሺ 900 እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለጊዘው ተጠርጣሪው ያመለጠ ሲሆን ተሸከርካሪው በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አክሎ ግልጿል፡፡

Visitors: Yesterday 55 | This week 845 | This month 2340 | Total 454549

We have 978 guests and no members online