ግምታዊ ዋጋቸው ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ፤

Posted in Latest News

User Rating: 5 / 5

Star activeStar activeStar activeStar activeStar active
 

ከግንቦት 1 እስከ 15/2009 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ገቢ እና ወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡ ሲገቡ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች 14 የተለያዩ መኪናዎች፣ ሞተር ሳይክሎች፣ ኤሌክትሮኖክስ፣ አልባሳትና ምግብ ነክ ሸቀጦች ሲሆኑ ግምታዊ ዋጋቸው ከ8 ሚሊየን 798 ሺ ብር በላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ሌላው ኮንትሮባንድ የተያዘበት ጣቢያ የአቤሎ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሲሆን 6 ተሸከርካሪዎች ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ መያዙን ግምታዊ ዋጋቸውም 1 ሚሊየን 290ሺ በላይ መሆኑን ገልፀው ለጊዜው ግምታዊ ዋጋው ያልታወቀ ዝንጅብል ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙንም ቅ/ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

በተያያዘ ዜናም በቡሌ ሆራ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 5 ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም 6 የጭነት ተሸከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ግምታዊ ዋጋቸውም 2 ሚሊየን 76ሺ ብር በላይ እንደሆነ ቅ/ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ፣ የኬላ ፈታሾች እና የክልል ፀጥታ አካላት ለኮንትሮባንዱ መያዝ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላት እንደሆኑ አቶ አዱኛ ነጋሳ የቅ/ፅ/ቤቱ ትምህርትና ድጋፍ አስተባባሪ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካላት ለጊዜው ማምለጥቸውን እና በህግ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በየሺወርቅ ተጫኔ

 

Visitors: Yesterday 89 | This week 469 | This month 1665 | Total 819632

We have 375 guests and no members online