አማካይ የቀን ገቢ ግምት መረጃ

Posted in Latest News

User Rating: 5 / 5

Star activeStar activeStar activeStar activeStar active
 

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከሚያዝያ 17 /2009ዓ.ም. እስከ ግንቦት 30 በንግድ ሱቆች ላይ ሲደረግ የነበረውን አማካይ የቀን ገቢ ግምት ጥናት መጠናቀቅ አስመልክቶ ከዝግጅት ተግባር አስከ ማጠቃለያ ምእራፍ ባለው የአፈጻጸም ሂደትና መረጃ አሰባሰብ ስርዓት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ባለስልጣን  መስሪያ ቤቱ  ቀደም ሲል አማካይ የቀን ገቢ ግምት  በ2003ዓ.ም በተደረገ ጥናት መሰረት እስካሁን ሲሰራበት መቆየቱን ገልጾ፤ አሁን ላይ በከተማው እያደገ ከመጣው ኢኮኖሚ ተመጣጣኝ ገቢ መሰብሰብ  እንዲያስችል፤የንግዱ ማህበረሰብ ከገቢው ላይ  የሚመለከተውን ግብር ወይም ታክስ በመክፈል ፍታሃዊ የታክስ ስርዓቱን በማስፈን ህጋዊውን ወደ ግብር መረቡ በማስገባትና ጤናማ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለመፍጠር፤ በዚህም ከከተማው አኮኖሚያዊ እድገት ጋር ተመጣጣኝ የልማት ስራዎችን በመተግበር የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል መሆኑን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ለስልጣን  የአዲስ አበባ ከተማ ታክስ ፕሮግራም ልማትና ድጋፍ ስራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ነጻነት አበራ ሰኔ9, 2009ዓ.ም ከሚድያ ተቋማት ጋር በተደረገ ውይይት ላይ አስታውቀዋል፡፡

የቀን ገቢ ግምቱ ቅሬታ እንዳይፈጥር ፣ የታክስ ህግ ተገዢነት ለመፍጠር፣  የታክስ አሰባሰብ ሰርቱን ፍታሃዊ ለማድረግ እና ከአድሎ የጸዳ መረጃ አሰባሰብ ስርዓት ለመፍጠር ከአንድ ሺ ዘጠኝ መቶ በላይ ከሶስት ሴክተር መስረያቤቶች ማለትም ከከተማ ከገቢዎች፣ ከንግድ እና ከፋይናንስ ቢሮ የተውጣጡ ገማቾች፣  ኢንስፔክሽን ና መረጃ አጣሪባለሙያዎች የስልጠና፣ የስምሪት አቅጣጫ ተሰጥቶ በተዘጋጀው መመሪያ መሰረት ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም በክፍለከተማና ወረዳ ደረጃ በስራ አስፈጻሚው መሪነት ሰራውን በጥብቅ ክትትልና ዲሲፕሊን ሲመራ ቆይቷል፡፡ በዚህም 148,756 የሚሆኑ ነጋዴዎች በቀን ገቢ ግምት መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን በግምቱ ወቅት 8,651 የሚሆኑ ህገወጥ ነጋዴዎች መገኘታቸው ተውቋል፡፡ 

በቅርብ ቀን የቀን ገቢ ግምት መረጃ ውጤት ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ይፋ እንደሚደረግ የተጠቆመ ሲሆን  የንግዱ ማህበረሰብ ቅሬታ ካለው ከወረዳ አስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ ባለው የቅሬታ ሰሚ ቡድን ማቅረብ እንደሚችል ተጠቁማል፡፡

   

 

Visitors: Yesterday 89 | This week 469 | This month 1665 | Total 819632

We have 342 guests and no members online