ከ 2 ሚሊዬን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃ መያዙ ተገለጸ፤

Posted in Latest News

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ግምታዊ ዋጋቸዉ 2 ሚሊዬን 116ሺ 61 ብር የሚያወጡ ኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡
ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች፣ ኮስሞቲክስ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ እርጥብ ጫት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ መድሃኒት  የተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሲሆኑ እቃዎች የተያዙት በብየቆቤ እና በሀረር የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከሰኔ 26/ እስከ ሃምሌ01/2009ዓ.ም ባሉት ቀናት መሆኑን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ትምህርት እና ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ዘቢደር በርሲሳ ገልጸዋል፡፡
እቃዎቹ ሊያዙ የቻሉትም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ አባላት፣ በክልሉ የጸጥታ አካላትና የአካባቢዉ ህብረተሰብ ባደረጉት ትብብር መሆኑን ወ/ሮ ዘቢደር አያይዘዉ ተናግረዋል፡፡   
በሌላ ዜና ወ/ሮ ዘቢደር በአዲሱ ገቢ ግብር እና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ዙሪያ በሐረር ከተማ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

Visitors: Yesterday 118 | This week 255 | This month 1971 | Total 822265

We have 226 guests and no members online