የክፍት ሥራ መደብ ማስታወቂያ

Posted in Vacancy

User Rating: 3 / 5

Star activeStar activeStar activeStar inactiveStar inactive

የኢትዮጵያ ገቢዎችን ጉምሩክ ባለሥልጣን በዋናው መ/ቤትና በሥሩ በሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶች በሚገኙ የሕግ ሙያ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ለክፍት ሥራ መደቦቹ የሚያመለክቱ ሥራ ፈላጊዎች፡-

1.   የተጠቃለለ የመመረቂያ ነጥባቸው ቢያንስ ወንዶች 2.5 እና ሴቶች 2.2 ያላቸው እና

2.   በሕግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸውና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ

መሆን አለባቸው፡፡

ስለሆነም ሥራ ፈላጊዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስት ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉ ስድስት ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ  ) ውስጥ፡- 

  • በየትኛውም ክፍት ስራ መደብ ላይ መቀጠር የሚፈልጉ ሥራ ፈላጊዎች መገናኛ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ “መ” 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ወይም በሚቀርባቸው የባለስልጣኑ ቅ/ጽ/ቤቶች መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እያሳሰብን፤ ቅ/ጽ/ቤቶቻችን በመቀሌ፤ በባሕርዳር፤ በሚሌ፤ በጋላፊ፤ በኮምቦልቻ፤ በጅግጅጋ፤ በድሬዳዋ፤ በሞያሌ፤ በጅማ፤ በሀዋሳ፤ በአዳማ እና በሞጆ ከተሞች የሚገኙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • ሥራ ፈላጊዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡  

 

ማሳሰቢያ፡-

1.   ሥራ ፈላጊዎች መቀጠር የሚፈልጉበትን አንድ ቦታ ብቻ በሥራ መጠየቂያ ቅፅ ላይ በግልፅ ማመልከት አለባቸው፡፡

2.   የፈተና ቀን፤ ቦታና ሰዓት በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት ለተመዘገቡ በዋናው መ/ቤት የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የሚገለጽ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶች ለመቀጠር ለሚያመለክቱ ሥራ ፈላጊዎች በተመዘገቡበት ቅ/ጽ/ቤት የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይገለጽላቸዋል፡፡ 

3.   ክፍት የሥራ መደቡ ፆታ አይለይም፡፡

4.   ሴቶች ይበረታታሉ፡፡

5.   ከምዝገባው ቀን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ሥራ ፈላጊዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


ተ/ቁ

የሥራ መደብ መጠሪያ

ደረጃ

ብዛት

የተፈላጊ ችሎታ መስፈርት

ደመወዝ

ሥራ መደቡ የሚገኝበት ቦታ

ትምህርት

 

ቀጥታ የሥራ ልምድ

1

ጀማሪ የሕግ ባለሙያ

7

7

በህግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ፣

0 ዓመት

9,246

ጂማ፤ ድሬዳዋ፤ ጅግጅጋ፤ ባሕርዳር፤ ኮምቦልቻ፤ ሞያሌ፤ ጋላፊ/ሚሌ ቅ/ጽ/ቤቶች

2

የሕግ ባለሙያ

8

1

በህግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ፣

2 ዓመት

13,184

ጋላፊ/ሚሌ ቅ/ጽ/ቤት

3

ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ I

9

8

በህግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ፣

4 ዓመት

15,743

ጂማ፤ ድሬዳዋ፤ ጅግጅጋ፤ ባሕርዳር፤ ኮምቦልቻ፤ ሀዋሣ፤ መቀሌ፤ ጋላፊ/ሚሌ ቅ/ጽ/ቤቶች

4

ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ II

10

10

በህግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ፣

5 ዓመት

18,137

ጂማ፤ ድሬዳዋ፤ ጅግጅጋ፤ ባሕርዳር፤ ኮምቦልቻ፤ ሀዋሣ፤ ሞያሌ፤ መቀሌ፤ አዳማ/ሞጆ፤ ጋላፊ/ሚሌ ቅ/ጽ/ቤቶች

5

የሕግ አገልግሎት ቡድን አስተባባሪ

11

1

በህግ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ፣

6 ዓመት

20,330

ጋላፊ/ሚሌ ቅ/ጽ/ቤት


 

Visitors: Yesterday 89 | This week 469 | This month 1665 | Total 819632

We have 353 guests and no members online